Ethiopia - ትራምፕ በኢራን አደገኛ ኦፕሬሽን | የነዳጅ እጦት በኢትዮጵያ | ኢራን ዩራኒየሟን ደበቀች | ሳውዲ የምስራች አሰማች

Feta Daily News www.youtube.com

አጭር ማጠቃለያ

ይህ የፈታ ዴይሊ ኒውስ ቪዲዮ በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት፣ የነዳጅ አቅርቦት ችግሮች እና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የተከሰተውን ውጊያ ጨምሮ ወቅታዊ ጉዳዮችን ይመለከታል።

  • ትራምፕ ኢራንን አስጠነቀቁ
  • በኢራቅ የጦር ጀት ተመታ
  • ኢራን ዩራኒየም መደበቋ ተሰማ
  • በኢትዮጵያ የነዳጅ እጥረት ተባብሷል
  • በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ውጊያ ተቀሰቀሰ
  • ኪም ጆንግ ኡን አዲስ ሚሳኤል ሞተር ሙከራን መሩ

ትራምፕ በኢራን ላይ ማሳሰቢያ ሰጡ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ካልተደራደረች "ድምጿን እንደሚያጠፉ" አስጠንቅቀዋል። ይህ ማስጠንቀቂያ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ በሄደበት ወቅት የወጣ ሲሆን ትራምፕ ከአዲሱ የኢራን አገዛዝ ጋር በጦርነቱ ማብቂያ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። የኢራን ባለስልጣናት ግን ድርድር ውስጥ እንዳልገቡ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ትራምፕ ኢራን የነዳጅ ኤክስፖርቷን 90 በመቶ የሚሸፍነውን የካርግ ደሴትን እንደሚያወድሙና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችንም እንደሚመቱ አስጠንቅቀዋል።

የጦር ጀት መውደም

በኢራቅ መሃመድ አላር በተባለ የጦር ሰፈር ላይ በተፈጸመ የሚሳኤል ጥቃት አንድ የኢራቅ ጦር ጀት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ጥቃቱ የተፈጸመው እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም ሲሆን የአየር ሃይሉን ንብረት አመድ አድርጓል። እስካሁን ድረስ ጥቃቱን የፈጸመው አካል በይፋ የታወቀ ነገር የለም፣ ነገር ግን በኢራን የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች ተጠርጣሪ ናቸው። ኢራን በይፋ ባትወስድም ጥቃቱ የመከላከያ ስልታችንን ለሚፈቱ ሃይሎች የተሰጠ መልዕክት ነው ብላለች።

ኢራን ዩራኒየም መደበቋ

አዲስ የደህንነት መረጃ እንደሚያመለክተው ኢራን 60 በመቶ የደረሰውን የዩራኒየም ክምችት ከጦርነቱ በፊት ሳታሸሽ እንዳልቀረች ነው። ዩራኒየሙ ወደ ኢስፋን የኒኩሌር ተቋም የተወሰደ ሲሆን ይህም ከመሬት በታች የሚገኝና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ተብሏል። መረጃው የሳተላይት ምስሎችን እና በኢራን ውስጥ ያሉ የሰው ምስክሮችን መረጃዎች መሰረት ያደረገ ነው።

በሳውዲ አረቢያ የቀይ ባህር የነዳጅ ምርት

ሳውዲ አረቢያ የሆርሙዝ ባህር መዘጋትን ተከትሎ ነዳጇን በቀይ ባህር በኩል ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ነው። በቀይ ባህር በኩል ያለው የነዳጅ ኤክስፖርት በቀን 7 ሚሊዮን በርሜል ደርሷል። ሳውዲ ነዳጅ ኤክስፖርት ማውጫውን ከሆርሙዝ ወደ ያንቡዕ ያዛወረች ሲሆን ነዳጁ በምድር በተዘረጋ መስመር ተጓጉዞ ወደ ቀይ ባህር ከደረሰ በኋላ በመርከቦች ይጓጓዛል።

በኢትዮጵያ የነዳጅ እጥረት

በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ የአንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች የአመት እረፍት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። በአዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች ነዳጅ ለማግኘት ረጅም ሰልፍ መጠበቅ ግድ ይላል። የናፍታ ተሽከርካሪዎች መቸገራቸውን አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ውጊያ

ከኢትዮጵያ ድንበር ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኝ ስትራቴጂካዊ ቀጠና ውስጥ ከባድ ውጊያ ተቀስቅሷል። በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በፌደራል መንግስት ኃይሎች እና በክልሉ ታማኝ ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ውጊያ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ስጋት አለ።

ኪም ጆንግ ኡን አዲስ ሚሳኤል ሞተር ሙከራን መሩ

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለአህጉር አቋራጭ ሚሳኤሎች ግብዓት የሚውልና ከፍተኛ ግፊት ያለው የጠንካራ ነዳጅ ሞተር ሙከራ በስኬት መከናወኑን አስታውቋል። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ሰሜን ኮሪያ የምታመነጫቸው ሚሳኤሎች ክብደታቸውን እንዲቀንስ እና ከየትኛውም ቦታ በፍጥነት እንዲተኮስ ያስችላቸዋል።

Summarize any YouTube video in seconds

Get summaries like this one for any video, in your language, with the free Summ app.

Download on the Apple Store
Get it on Google Play

Transcript

YouTube Transcript Generator

0:12 ሰላም ጤና ይስጥልን የተከበራችሁ የፈታ ዲሊ ቤተሰቦች የሰአቱን መረጃ ይዘን ተገኝተናል። እንደተለመደው አንኳር ጉዳዮችን በቅድሚያ በማስተዋወቅ ወደ ዝርዝሩ እናልፋለን። አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያካሄዱት ጦርነት በቀጠለበት ሁኔታ ከዚሁ ጎን ለጎን ከኢራን አመራሮች ጋር ድርድር ተቀምጠናል የሚሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ለትም ኢራንን ተደራድረሽ ካልተስማማሽ ድምጥ ማጥሽን እንደማጠፋሽ ማሳወቅ እወዳለሁ ሲሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይፋ አድርገዋል። ኢራን ዛሬም ስለ ድርድር የማውቀው ነገር የለም ጦርነት ላይ ነኝ ስትል አስታውቃለች። ከዚህ ውጪም ትራምፕ ይቅርቦት የተባሉትን አደገኛ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በኢራን እያሰቡ ነው ተብሏል። ቢሲ እና ቦር ስትሪት ጆርናል መረጃውን ይፋ አድርገውታል እኛም ይዘነዋል። ዓለምን ያስደነገጠ ወታደራዊ ክስተት ተከስቷል። በከፍተኛ ሚስጥር

0:57 በተያያዘ እና ስትራቴጂካዊ በሆነ የጦር ሰፈር ላይ በተሰ ተስነዘረ ድንገተኛ የሚሳይል ናዳ የጦር ጀት ሙሉ በሙሉ ወደ አመድነት ተቀይሯል። ጥቃቱ የተፈጸመው እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የሚሳይ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሲሆን በጀቱ ላይ የደረሰው ጉዳት የጦር ሃይሉን የአየር የበላይነት ክፉኛ መቶታል። መረጃ የምሽቱ ጥንቅራችን አካል ነው። አዲስ የደህንነት መረጃ ኢራን ተብላቶ የተቀመጠ የዩራኒየም ክምችቷን ከጦርነቱ በፊት ሳታሸሽ እንዳልቀረች አመለከተ። የትራምፕ አስተዳደር 31ኛ ቀን የደፈነውን ጦርነት ለማስቆም ካቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ኢራን ስልሳ በመቶ ደረጃ የደረሰውን የዩራኒየም ክምችቷን እንድታስረክብ የሚል ነው። ንጥረ ነገሩ ታዲያ በኢራን ደህንነት ወደ ሌላ ተቋም ስለመወሰዱ የሳተላይት መረጃ ጠቁሟል። ሳውዲ የሆርሙዝ መዘጋትን ተከትሎ ነዳዋን በቀይ ባህር በኩል ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ትገኛለች

1:44 ከቀን ወደ ቀን ነዳጅ በቀር የማሻገር አቅሟን እያሻለች ሲሆን አሁን ላይ በቀይ ባህር በኩል ያለው ነዳጅ ኤክስፖርት የማድረግ አቅም በቀን 7 ሚሊዮን ብር ሜል መድረሱን አሳውቃለች ነገሩ ነዳጅ ጭንቅ ለሆነበት አለም መልካም ዜናው ነው ተሰምቷል በመካከለኛው ምስራቅ በአሜሪካ እስራኤል እና ኢራን መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ተከትሎ አለም አቀፉ የነዳጅ አቅርቦት እና የዋጋ ሁኔታ ከባድ ቀውስ ውስጥ ገብቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በበርካታ ሀገራት የነዳጅ እጥረት እየተከሰተ ይገኛል። የነዳጅ እጥረቱ ኢትዮጵያንም ጭምር አስፍቶ መነካካት ጀምሯል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ጥንቅራችን አጠር አድርጎ የሚያደርሳችሁ እለታዊ መረጃ ይኖራል። ከኢትዮጵያ ድንበር ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኝ ስትራቴጂካይ ቀጠና ውስጥ ዛሬ ረፋዱን ከባድ ውጊያ ተቀስቅሷል። በተሰነዘሩት የድሮን ጥቃቶች እና በምድር ላይ የሚሰማ የከባድ መሳሪያ ድምጽ ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢ ያለውን ጥረት

2:31 አባብሷል። መረጃውን እናደርሳለን ሰሜን ኮሪያ ሌላ አስጊ መሳሪያ መዘዘች ኪም ጆንጉን ለአሜሪካ ስጋት ነው የተባለ አዲስ የሳይል ሞተር ሙከራ ሲመሩ ታይተዋል መረጃውን አጠር አድርገን ይዘናል እስከ ጥንቅራችን ፍጻሜ አብራችሁን ቆዩ የምንለቃቸው እለታዊ ትኩ ዜናዎች እንዲደርሳችሁ ላይክ ሼር ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳትረሱ ትራምፕ በኢራን አደገኛ ኦፕሬሽን ይፋ አደረጉ። አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያካሄዱ ጦርነት በቀጠለበት ሁኔታ ከዚህ ጎን ለጎን ከኢራን አመራሮች ጋር ድርድር ተቀምጠናል የሚሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራም በዛሬው ለትም ኢራንን ተደራ አድረሽ ካልተስማማሽ ድምጥ ማጥሽን እንደማጠፋሽ ማሳወቅ እወዳለሁ ሲሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ይፈርገዋል። ፕሬዝዳንቱ በዛሬው እለት በትሩዝ

3:18 የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት በዚሁ ጥብቅ የማስጠንቀቂያ መልዕክታቸው ጦርነቱ ጦርነቱ በሚያበቃበት ጉዳይ ላይ አዲስ ካሉት የኢራን አገዛዝ ጋር በጥብቅ ውይይት ላይ ነን ያሉ ሲሆን ይህ የሚጠበቀው ውይይት ተገቢውን ውጤት ካላመጣ ግን በአጸፋ የምንወስደው እርምጃ እጅግ የከፋና ቀላል የማይባሉ ውድመትን ጭምር የሚያስከትል ነው ሲሉም አጥብቀው አስጠንቅቀዋል። የኢራን ባለስልጣናት በወዳጅ ሀገራት በኩል መልዕክት ከመለወጥ ውጪ በአሜሪካ በኩል እንደሚባለው ድርድር ውስጥ የገባንበት ሁኔታ የለም በሚል በተደጋጋሚ የተነገረ ሲሆን በዛሬው ለትም የራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጊ በፓኪታን በኩል በኩል አቋማችን በማሳወቅ መልዕክት ከመላወጥ ውጪ ኢራን ድርድር ውስጥ የገባችበት ሁኔታ እንደሌለ መታወቅ አለበት ሲሉ በሰጡት መግለጫ ደግሞ አስታውቀዋል። ትራምፕ የቀድሞ የኢራን አገዛዝን እንደዚሁም ከዚያ በኋላ በዚሁ አገዛዝ የተተካውን አመራር ካላስወገድነው

4:03 አሁን ለድርድር የተቀመጠው ከሶስተኛው ትውልድ አመራር ጋር እንደሆነ መታወቅ አለበት ሲሉም አስታውቀዋል። ድርድር እየተካሄደ ነው። የለም አልተካሄደም የሚለው ጉዳይ በስፋት እያወዛገበ ባለበት በዚህ ሰዓት ትራምፕ ከኛ ጋር ተደራድራቸው አንዳች አይነት መግባባት ላይ የማትደርሱ ከሆነና በዚህም የድርድር ውጤት የተዘጋ የኦርሙዚ መጥ የማይከፈት ከሆነ ብሔራን የነበረን ቆይታ እጅግ አሳዛኝ በሆነ ታሪክ የሚጠናቀቅ መሆኑን ልታውቁት ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አጥብቀው ያስጠነቀቁበት ሁኔታ ታይቷል። ማስጠንቀቂያው በውስጡ ምን ይዟል የሚለውን በተመለከተ ትራምፕ ሊከተል ይችላል ያሉትን ጥፋት አንድ ሁለት ብሎ በዝርዝር አሳውቀዋል። ትራምፕ የሰጡት አንደኛው ማስጠንቀቂያቸው ያናቸውን የጣሉባትን የኢራን 90 በመቶ የነዳጅ ኤክስፖርት የሚዘጋጅባትን የካርግ ደሴትና ውድማት አለን የሚሉ ታይቷል። ትራም ፉከራቸውና የማስፈራሪያ ማስጠንቀቂያቸው በዚህ አላበቃ። ከዚህ ቀድ ቀደም

4:49 ጥንቅ አድርገን አውድመን ኢራንን ጨለማ ውስጥ እናስቀምጣታለን ያሉት የኢራን ኤሌክትሪክ ሃይል መሰረተ ልማቶችንም ዛሬም ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ዛቻን አስምተውበታል ትራምፕ በዚሁ የዛሬው ህዝብ መልክታቸውም በአፋጣኝ ወደ ስምምነት የማይደረስ ከሆነ እስከ ዛሬ ድረስ ወንብለን ሳንነካኝ ሆኖን የኢራን ኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጥንቅ አድርገን በማውደም በኢራን የነበረንን ቆይታ በዚያው የምናጠናቅቅ መሆኑ ይታወቅልን ሲሉም ትራምፕ በዚሁ የትሩዝ የማህበራዊ ትስስር ገጽ መልእክታቸው ላይ አስታውቋል። ትራምፕ በዚችው በነዳጅ ሀብት በተንበሸበሸችው የራን ካርግ ደሴት ላይ አንድ ጊዜ በወታደርጉ እቆጣጠራታለሁ። ሌላ ጊዜ ደግሞ አውድማታለሁ በሚለው ዛቻቸው እንደቀጠሉ ናቸው። ከአርግደሴትን ጨምሮ የትኛውንም ሄራን ግዛት በእግረኛ ጦር ለመቆጣጠር የሚደረግ ማናቸውም እንቅስቃሴ የአሜሪካንን እግረኛ ጦር ከባድ ዋጋ ያስከፍለዋል በሚል በአሜሪካውያን በኩል ከባድ ተቃውሞ እየቀረበበት ይገኛል። ስልሳ አምስት በመቶ አሜሪካውያን

5:36 የእግር ውጊያ የሚለውን አጥብቆ እንደሚቃወሙ የዛሬው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ዘገባ አመልክቷል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማህል ኢራን የሚገኘውንና በተራሮች ስር ተደብቆ ይገኛል የሚባለውን የኢራን ዋነኛ ኒኩሌ ግብዓት የሆኑ የበለጠገ ዩራኔ ምን ጭምር በልዩ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን የመቆጣጠር እቅድ እንዳላቸውም የዛሬው የወልት ዘገባ አመላክቷል። ቢቢሲና ኒውዮርክ ታይምስም ይሄንኑ መረጃ ተቀባብሎታል። ኒውዮርክ ታይምስ በዘገባው ትራምፕ በይስፋን ውስጥ በሚገኝ ተራራ ስር በብዛት ተከማችቶ እንደሚገኙ የሚታመኑ ቦንብ ለማምረት የቀረቡ የኒኩየር ቁሶችን ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት የሚያስችል ዘመቻ ለማካሄድ በግል እያሰቡ ነው ብለዋል። ትራምፕ ቬንዚላ ላይ ፕሬዝዳንት ማዶሮን ለመያዝ በተሰራው ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን የተበረታቱ ይመስላል ሆኖም አስተያየት ሰጪዎች ኢራን ቬንዚል አይደለችም ትራምፕ ይሄው ልዩ ኦፕሬሽን ቢቀርባቸው ይሻላል የሚል በሚል ምክር ሃሳባቸውን እየለገሱ ይገኛሉ። ከሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ መዋጮ ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንት

6:24 ዶናል ትራምፕ ከዚህ ቀደም ከፍ ዝቅ ያደረጓት አውሮፓቷ ስፔን ከኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክፉኛ ያምርራለች። ስፔን በኢራን ላይ ጥቃት ነው የሚፈጽሙ የአሜሪካ አውሮፕላኖች በግዛት ያቋርጠው ማለፍ የለባቸውም በማለት የአየር ክልሏን የዘጋጅ መሆኗን የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስተር ማርጋሪ ሮቤልስ እንዳስታወቁ የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል። የስፔኤል መንግስት እርምጃ በዚህ አላበቃ። ከኢራን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ጋር በተያያዘ የአሜሪካ ጦር በግዛት የሚገኙትን የጦር ሰፊ ሰፈሮች መጠቀም የለበትም በማለትም ጥብቅ ትእዛዝን ጭምር እንደሰጠች ዘገባው አክለው አመላክቷል። ሚኒስትሯ ጨምሮም አሜሪካ በስፔን ግዛት ውስጥ የሚገኙ የጦር ሰፈሮቿን ከኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ ጥቅም ላይ እንዳታውል ማዘዛቸውንና ይህንንም ከመጀመሪያው ለአሜሪካ መንግስት አስታውቀናል ብለዋል። ይህ በእንዲለ ሌላኛው የኢራን እና የህዝብ ወላ ተፋላሚ እስራኤል በዚሁ ፍልሚያው አዛሪ የቀጥለች ሲሆን ወታደሮቿ ወደ ደቡባ ሊባኖስ በጥልቀት በመግባት እና ሰፊ የሊባኖስን ግዛት ይዘው

7:11 የመከላከያ ወረዳን ለመመስረት በከባድ ፍልሚያ ላይ ይገኛሉ። በዛሬው እለትም በእስራኤል የወደብ ከተማ ሃይፋ በሚል የሚገኘው የእስራኤል ግዙፍ ነዳጅ ማጣሪያ ለሁለተኛ ጊዜ እሳት ተነስቷል። ይሄው እሳት እንዴት ሊከሰት ቻል የሚለው ጉዳይ እያነጋገረ ነው። ከሊባኖስ ሆኖ ሮኬቶችን በሚያስፈነጭፈው ህዝብ ወላነው ወይስ በኢራን ሚሳኤል የሚለው ጉዳይ ግልጽ አልሆነም። በቀጣይ መረጃ የጦር ጀቱ በሚል ተመት ተወደመ። አለምን ያስደነገጠ ወታደራዊ ክስተት ተከስቷል። በከፍተኛ ሚስጥር በተያያዘና ስትራቴጂካ የጦር ሰፈር ላይ በተሰነዘረ ድንገተኛ የሚሳሳይ ናዳ የጦር ጀት ሙሉ በሙሉ ወደ አመድነት ተቀይሯል ጥቃቱ የተፈጸመው እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የሚሳይ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሲሆን በጀቱ ላይ የደረሰው ጉዳት የጦር ሃይሉን የአየር ላይ የበላይነት ክፉኛ መቶታል ዛሬ ረፋዱን ከኢራቅ የተሰማው ዜና

8:00 በባዳድ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኘው መሃመድ አላር ሰፈር ላይ በድንገት በተሰነዘረ የሚሳይ ጥቃት አንድ የራቅ የጦር ጀት ሙሉ በሙሉ መውደሙን አመልክቷል። ይህ ጥቃት የተፈጸመው እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም ሲሆን የአየር ሃይሉን ንብረት አመድ አድርጎታል። የራቅ መከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱን ያረጋገጠ ሲሆን ክስተቱ በቀጠና ያለውን የደህንነት ስጋት ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮታል። በባዳድ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኙ መሀመድ አላ የጦር ሰፈር ላይ የተሰነዘረውንና የጦር ጀት ያወደመውን የሚሳይ ጥቃት ሮይተርስ እና አሶሺድ ፕሬስ የዜናው ኪሎች በጥቃቱ ዙሪያ ያሉ ወታደራዊ ዝርዝሮችም እጮቻቸውን ጠቅሰው አረጋግጠዋል። የራ አብዮታዊ ዘበኛ ደግሞ ጥቃቱን ተከትሎ በሰጠው የዛቻ ምላሽ ቀጠናዊ ጥረቱን ይበልጥ አጋግሎታል። በአግዳድ በሚገኘው የጦር ሰፈር ላይ ለደረሰው እና የኢራን የጦር ጀትን ላወደመው የሚሳሳይ ጥቃት እስካሁን ድረስ የትኛውም አካል በይፋነቱን አልወሰደም።

8:45 ብሄራዊ በኢራቅ ውስጥ የሚንቀሳቀሱና በኢራን የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች በአካባቢው በሚገኙ የመንግስት እና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ተደጋጋሚል እና የድሮን ጥቃቶችን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። የዛሬውም ጥቃት የነዚህ ቡድኖች እጅ ሊኖርበት እንደሚችል በስፋት ይገመታል። ኢራለ ጥቃቱ በይፋት ባትወስድም ጥቃቱ የተፈጸመው የመከላከያ ስልታችንን ለሚፈቱ ሃይሎች የተሰጠ ቅምሻ ነው የሚል አንድምታ ያለው መልዕክት ታስተላልፋለች። ይህ መግለጫ በተለይ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ ነጣጠረ ሲሆን በቴራም በኩል ያለው ወታደራዊ ዝግጁነት ወደ ቀይ መስመር መድረሱን ያሳያል። በአንጻሩ አዋሽንግተን እና ቴሌ አቢቭ በጥቃት ጥቃቱ ዙሪያ ጥብቅ ሚስጥራዊን መርጠዋል። አሜሪካ በቀጠና ያሏት የራዳር እና የጸረ ሚሳኤል ስርአቶች ጥቃቱን መከላከል አለመቻላቸው ትልቅ የደህንነት ስብራት እንደሆነም ተንታኞች ይገልጻሉ።

9:33 በቀጣይ ርዕስ ኢራን ዩራኒየሟን ሳታሸሽ አትቀርም። አዲስ የደህንነት መረጃ ኢራን ተብላቶ የተቀመጠ የዩራኔም ክምችቷን ከጦርነቱ በፊት ሳታሸሽ እንዳልቀረች አመለከተ። የትራምፕ አስተዳደር ዛሬ 31ኛ ቀን የደፈነውን ጦርነት ለማስቆም ካቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ የራን 60 በመቶ ደረጃ የደረሰውን የዩራኔም ክምችቷን እንድታስረክብ የሚል ነው። ባለፈው አመት በእስራኤል ኢራን የ1 ቀናት ጦርነት ወቅት የኢራኑ ኒኩሌ ተቋማት በአሜሪካ ጭምር መደብደባቸው ይታወሳል። ድብደባውን ተከትሎ የኢራን የተብላ ዩራኔ ውድመት ከደረሰባቸው የኒኩየር ተቋማት ፍርስራሽ ስር እንደሚገኝ ከዋሽንግተን ሲነገር ይሰማል። ኢራን ግን ከ12 ቀኑ ጦርነት ወዲህ በሶስት ዋነኛ የኒኩየር ተቋማት ላይ መልሶ ግንባታዎችን ስታካሄድ መቆየቷ ሲነገር ነበር። አሁን የወጣ የደህንነት መረጃ መረጃ ደግሞ ኢራኔ ይሄንን እንድታስረክብ ከአሜሪካ ቅድመ ሁኔታ የቀረበበትን ዩራኔም ቀድማ

10:19 ሳታሸሽ አልቀረችም ይላቶሚክ ሳይንቲስቶች የሚታተም አንድ የመረጃ ምንጭ ነው ይሄንን የጠቆመው 10 የኒኩየር ቦምብ ለመስራት ያስችላል የተባለለት ከአራት መቶ አርባ ኪሎ ግራም ዩራኒየም በደህንነት ኦፕሬሽን ከነበረበት ወደ ሌላ ስፍራ መወሰዱን ጽሁፎ አትቷል ዩራኒየሙ ኢራን ካሏት የኒኩየር የምድር ስር ተቋማት መካከል ጥልቅና ደህንነቱ በእጅግ ወደተበቀለት ኢስፋን የኒኩየር ተቋም ተወስዷል ነው የተባለው ጥናቱ የሳተላይት ምስል መረጃዎች ጥናት ላይ የተመሰረተ ሲሆን በኢራን ውስጥ ያለው የሰው ምስክር መረጃዎችንም እንደማce አቅርቧል። ዩራኒሙ በቅድሚያ በናትታንስ እና ፎርዶ ኒክሌ ተቋማት ውስጥ እንደነበር የተጠቆመው በመረጃው አሜሪካው ሙሉ በሙሉ ድመረስኩ ካለችባቸው ተቋማት ከድብደባ መልስን ክምችቱን ማሸሻ ነው የገለጸው። እንደ ደህንነት መረጃው ባለፈው አመት ወር ላይ በናታን ዜኒኩየር ተቋም አከባቢ ከፍተኛ ስብስቦ የሆነ ትራፊክ ፍሰት እና የጭነት ጉዞ እንደነበር

11:07 መመልከቱን ይፋ አድርጓል። የጭነቱ መዳረሻም በጥልቀት ምድር ውስጥ ከተራራ ስር በተሰራው ኢስፋ የኒኩየር ተቋም መሆኑን አመልክት አመልክቷል። ወደ ቀጣይ ረሳለፍን። ከሳውዲ ስለ ነዳጅ ለአለም የተነገረው መልካም ዜና ሳውዲ በቃይ ባህር የነዳጅ ምርታ እጥፍ አደረገች። ሳውዲ የሆርሙዝ መዘጋትን ተከትሎ ነዳጅዋን በቀይ ባህር በኩል ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። ከቀን ወደቀን ነዳጅ በቀኝ ባህር የማሸጋገር አቅሟን እያሸጋ አሻሻለች ሲሆን አሁን ላይ በቀይ ባህር በኩል ያለው ነዳጅ ኤክስፖርት የማድረግ አቅም በቀን 7 ሚሊየን በርሜል መድረሱን አሳውቃለች። ሳውዲ ነዳጅ ኤክስፖርት ማውጫውን ከሆርሙዝ ወደ ያንብ ወደ

11:54 አዛወረች ሲሆን በምድር በተዘረጋ መስመር ነዳጁ ተጓጉዞ ወደ ቀይ ባህር ወደ ከደረሰ በኋላ በነዳጫ መርከቦች እንዲጓጓዝ ይደረጋል። ይሄ መስመር ግን የሆርሙዝ ሰርጥን መስመርና በቀላ ገበያ የሚቀርበውን አቅም በፍጹም የሚጠጋ አይደለም። ሆኖም ከጦርነቱ በፊት በያምንቦ ወደብና መሰረተ ልማቱ በኩል 5 ሚሊዮን ብር ሜል ነዳጅ ብቻ ይጓጓዝ የነበረ ሲሆን ባለፉት ሁለት ሳምንታት ሳውዲ ባደረገችው ፈጣን የመሰረተ ልማት ተጨማሪ ማስፋፊያ ጥረት አሁን ላይ በቀይ ባህር ማሻገር የምትችሉ የነዳጅ መጠን ከአምስት ወደ ሰባት እንዲሁም በቀጣይ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ሜል እንደሚደርስ ነው የተነገረው። ለሳውዲ ነዳጅ ምርት ቅርብ የሆነ ምንጭ ጠቅሶ አሶሺ ፕሬስ ባወጣው ዘገባ ሳውዲ በየቀኑ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚል ድፍድፍ ነዳጅ በቀኝ ባህር ስታወጣ ከዚህ ውስጥ 2 ሚሊዮኑ በሳውዲ ነዳጅ ማጣሪያዎች ውስጥ ያለፈ ወይም የተጣራ ስለመሆኑ ተገልጿል። ሳውዲ በሆርሙዝ በኩል ታወጣ የነበረው እለታዊ ነዳጅ

12:39 ምርት ግን 15 ሚሊዮን ብር ሜል ነበር ይታወቃል። የያምቡ መስመር መስመር በጦርነቱ ያለ የነዳጅ ዋጋ ወደ 200 ዶላር እንዳይደርስ ካደረጉ አማራጮች መካከል መሆኑ ተገልጿል። ሆኖም በሳምንቱ የየመኖች ውጤት ጦርነቱን ወደቀ የባህር መሳብ ድርጊት ይህንን የሳውዲ ጥረት አረጋ ውስጥ መጣሉ እና ችግሩን የሚያወሳስ መሆኑ ተነግሯል። በኢራኑ ጦርነት ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ መሳተፉን ወደ እስራኤል ሚሳኤል በማስወንጨፍ አውጇል። ሁቲ በጋዛ ጦርነት ወቅት የእስራኤል እና ከእስራኤል ጋር ትስስር ያላቸው መርከቦች ላይ ጥቃት ሲሰነዝር ይታወሳል። አሁን በይፋ እስራኤል ነው ያጠቃ ሲሆን በባቢል ማንዴብ በነዳጫ የመርከቦች ጥቃት ስለመሰንዘር ግን በይፋ የገለጸው ነገር የለም። ሳውዲ ቡድኑ ወደ ጦርነቱ እንዳይገባ ለማድረግ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ስታደርግ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

13:28 ወደ ቀጣይ መረጃ አለፍን። በኢትዮጵያም የተከሰተው የነዳጅ እጥረት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ የአንዳንድ መንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች የአመት እረፍት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ቢሲ ያነጋገራቸው ሰራተኞች ተናገሩ። ከዚህም በተጨማሪ አሁን ከተፈጠረው አለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስና እጥረት ጋር በተያያዘ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች ነዳጅ በማዳዎች ለመቅዳት እጅግ ፈታኝ መሆኑንም ዘገባ አመላክቷል። በርካታ ማዳዮች ከነዳጅ ውጪ ሲሆኑ በተወሰኑት ነዳጅ ባለባቸው አካባቢዎች ነዳጅን ለመቅዳት ሰዓታት የሚፈጅ ረጅም ሰልፍ መጠበቅ ግድ እንደሚልም ዘገባ አመላክቷል። ቢቢሲ አማርኛዉ ድረገጽ በዚህ የዛሬው ዘገባው በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ተከትሎ ናፍታ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች መቸገራቸውን ያነጋገርኳቸው አሽከርካሪዎች ነግረውኛል ብለዋል። በዚህም በአዲስ አበባና ሃዋሳ የሚገኝ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ለመኪኖቻቸውን አፍጣ ለመቅዳት

14:14 እስከ ሶስት ቀናት ድረስ በነዳጅ ማዳዎች ዙሪያ በመሰለፍ ለመጠበቅ መገደዳቸውን መረጃውን እንዳደረሱትም ቢሲ በዚሁ ዘገባው አክለው አመላክቷል። በዚህም የተነሳ ተማሪዎችን የሚያመላልሱ ወደ አዲስ አበባ ለተለያዩ ጉዳይ የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች መቸገራቸውን አስረድተዋል። በተጨማሪም ይህ እጥረት ወደ ቤንዚን ይሸጋገራል የሚል ስጋት መኖሩንም የተሽከርካሪ ባለቤቶች ጨምረው እንደገለጹለት ቢሲ በዚሁ ዘገባ አክለዋል። በመካከለኛውም ስራ የሚካሄደውን ጦርነት ተከትሎ የአለም አንድ አምስተኛ የሚሆን ነዳጅ የሚተላለፍበት የኦሮሞ ሰርጥ መዘጋቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት ከማድረግ ባሻገር አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ቅድመ ጦርነት ከነበረበት በ70ዎቹ ዶላር ከሚገኝበት በአሁኑ ሰአት ከ1 ዶላር በላይ ደርሷል አሁን የተከሰተውን አለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ተከትሎ የተለያዩ

15:00 ሃገራት ከቁጠባ ጀምሮ የተለያዩ ችግሩን ሊያሻግሩ ይችላሉ ያሏቸውን እርምጃዎች እየወሰዱ ይገኛሉ ወደ ቀጣይ መረጃ አለፍን። ድንገተኛ የድሮን ድብደባ እና ዛሬ የፈነዳው ጦርነት ከኢትዮጵያ ድንበር ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኝ እጅግ ስትራቴጂካይ ቀጠና ውስጥ ዛሬ ረፋዱን ከባድ ውግያ ተቀስቅሷል። በተሰነዘሩት የድሮን ጥቃቶች እና በምድር ላይ የሚሰማው የከባድ መሳሪያ ድምጽ ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢ ያለውን ውጥረት አባብሶታል። በደቡብ ምዕራብ ሶማልያ ዋና ከተማ በአይደዋ ውስጥ በፌደራል መንግስት ኃይሎች እና በክልሉ ታማኝ ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ከፍተኛ ውጊያ ቀጠና እንድምታው ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም እና ከሰላም አስከባሪ ያለው እንቅስቃሴ ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ሆኗል። በአይደዋል ለኢትዮጵያ የድንበር ደህንነት

15:47 ስትራቴጂካ ጠቀሜታ ያላት ከተማ ከመሆኑ አንጻር በከተማ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው ጫና ከፍተኛ ነው። ኢትዮጵያ በሶማሊያ በአፍሪካ ብረት የሽግግር ተልዕኮ አትሚስና በሁለትዮች የስምምነት መሰረት በባይደዋና አካባቢዋ በርካታ ቁጥር ያለው ሰራዊት አሰማርታ ትገኛለች። የዛሬ ውጊያ የኢትዮጵያን ጦር አታብቂኝ ውስጥ የከተተም እንደሆነ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች አመልክተዋል። ከአንከራው ድርድር በኋላ በፕሬዝዳንት አሰንሼ የሚመራው የሶማልያ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነት ያለው ሲሆን የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ፕሬዝዳንት አብደ አዚዝ ላፍታጋሪን የኢትዮጵያ የቅርብ ወዳጅ እና የጸረ አልሸባብ ትግል አጋርም ናቸው። በዛሬው ውጊያ የኢትዮጵያ ሰራዊት እስካሁን በገለልተኝነት ቢቀጥልም ግጭቱ እየተባባሰ ከሄደ እና የላፍታ ጋር አስተዳደር አደጋ ላይ ከወደቀ ኢትዮጵያ ዝምብላ እንደማትመለከት የፖለቲካ ተንታኞች ይገምታሉ። በቱርክ ድሮኖች የታገዙ የዛሬው ፌደራል መንግስቱ ጥቃት

16:34 የኢትዮጵያን ጦር የደህንነት ቀጠና ወይም በፈር ዞን ሊያናጋ ይችላል የሚል ስጋት አለ። ውጊያዊ አልሸባብ ክፍተቱን ተጠቅሞ ወደ ከተማዋ እንዲገባ መንገድ የሚከፍት ከሆነ የኢትዮጵያ ጦር የድንበር ጥሰትን ለመከላከል ሲል ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ውስጥ ሊገባ እንደሚችልም ተንታኞች አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ጦር በከተማው ያለውን ስልታ ይዞታ ማጠናከሩና የሁለቱን ወገኖች እንቅስቃሴ በጥንቃቄ እየተከታተለ ይገኛል። ይህ ግጭት ከመቀስቀሰው አንድ ቀን ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮኖች በፑንትላንድ ርዕሰ መዲና ጋዌ በመገኘት ከፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒ ጋር መወያየታቸው ታውቋል። በባይዲዋ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ በሶማሌ ውስጣዊ ግጭቶች ጣልቃ እንደማይገባ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ከአንድ ሳምንት በፊት በደቡብ ምዕራብ ሶማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያሰለጠናቸውን የክልሉ ልዩ ሃይሎች ማስመረቁ ይታወሳል። በወቅቱ የክልሉ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ መንግስት ለሰጠው የወታደራዊ

17:20 የስልጠና ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርቦ ነበር። ወደ ቀጣይ መረጃ አለፍን። ኪም ጆንጉል ለአሜሪካ ስጋት የሆነውን አዲስ የሚሳይ ሞተር ሙከራ በበላይነት መሩ። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንጉን ለሀጉር አቋራጭ ሚሳሎች አይ ሲቢኤም ግብዓት የሚውልና ከፍተኛ ግፊት ያለው የጠንካራ ነዳጅ ሶሊድ ፊውል ሞተር ሙከራ በስኬት መከናወኑን አስታውቋል። የሃገሪቱ የመንግስት ሚዲያ እንደዘገበው ይህ የከርሰ ምድር የሞተር ሙከራ እስከ 2500 ኪሎ ኒውተን የሚደርስ የግፍ ግፊት ሃይል ያስመዘገበ ሲሆን በግንባታው ላይም እጅግ ዘመናዊ ካርበን ፋይበር ግብዓቶች ጥቅም ላይ ውለዋል። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ሰሜን ኮሪያ የምታመነጫቸው ሚሲያልሎች ክብደታቸውን እንዲቀንስ እና ከየትኛውም ቦታ በፍጥነት እንዲተኮስ

18:07 የሚያስችላቸው ነው። ይህም የአሜሪካ መከላከያ ስርአት ሚሳሎቹ ሳይተኮሱ አስቀድሞ ለመለየት ያለውን ጊዜ በእጅጉ እንደሚያሳጥረው ተገልጿል። ኪምንጉን በሙከራው ወቅት ባደረጉት ንግግር ሀገራቸው ያላትን ስትራቴጂካ የወታደራዊ ሃይል ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የታለመ መሆኑን እና ማንኛውንም የአሜሪካን ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጧል። ከሰሞኑ ኪም በሀገራቸው ፓርላማ አፍቀርበው ሰሜን ኮሪያ በማይቀለበስ ደረጃ የኒኩሌ መሳሪያ ባለቤት መሆኗን ማረጋገጣቸው ይታወሳል። የኢራኑ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የሰሜን ኮሪያው መሪ ከልጃቸው ጋር ሆነ የጦራቸውን አዳዲስ አቅሞች በማሳየት ላይ ይገኛሉ። ውድ ቤተሰቦቻችን ለዛሬ ያዝንላችሁን ርዕሰ ጉዳዮች እዚህ ላይ ቋጭን። ላይክ፣ ሼር እና ኮሜንት በማድረግ ለቻናላችን ድጋፋችሁን መግለጽ እንዳትዘነጉ እያልን ከሌሎች መረጃዎች ጋር ደግመን እስክንገናኝ ቸር ያሰማን ስንል ተሰናበትን።

Share

YouTube Video Summaries