አጭር ማጠቃለያ
ይህ ቪዲዮ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት፣ በተለይም ሱዳን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነት እና በኤርትራ ነፃነት ላይ ያሳደረችውን ተጽዕኖ ይመረምራል። በተጨማሪም ደቡብ ሱዳን ከሱዳን በመገንጠል ሱዳን ያጣችውን የነዳጅ ሀብትና የግብፅን ተጽዕኖ ያብራራል።
- ሱዳን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ገብታለች።
- ሱዳን የኤርትራን ነፃነት ደግፋለች።
- ደቡብ ሱዳን ከሱዳን በመገንጠል ሱዳን የነዳጅ ሀብቷን አጥታለች።
- ግብፅ በሱዳን ላይ ተጽዕኖ አላት።
የኢተርስ ዘገባና የሱዳንና ኢትዮጵያ ታሪክ
ኢተርስ በትላንትናው እለት ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት ከኢትዮጵያ ጋር በማያያዝ አንድ ዘገባ አውጥቷል። ዘገባው የኢትዮጵያ መንግስት ለአንደኛው የሱዳን ተፋላሚ ኃይል የስልጠና ቦታ በመስጠት ድጋፍ እያደረገ ነው ይላል። የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። ነገር ግን ይህ ዘገባ እንደተጠበቀ ሆኖ የሱዳንና የኢትዮጵያ ታሪክ ሲፈተሽ አንዳንድ መራራ እውነታዎች ብቅ ይላሉ።
የሱዳን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት
ሱዳን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት የጀመረችው ዛሬ አይደለም። ሁለቱም አገራት በታሪካቸው በርካታ የእርስ በርስ ጦርነቶችን አስተናግደዋል። በተለይም ሱዳን ከህወሃት ጀምሮ እስከ ኤርትራ ተገንጣይ ሃይሎች ድረስ ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ እንዲሁም መተላለፊያ ኮሪደር በመፍቀድ የኢትዮጵያን የእርስ በርስ ጦርነት አቀጣጥላለች። የሱዳን መንግስታት በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ታሪክ እንዳላቸው የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠሩ የሰሜን ጦርነቶች የሱዳን መንግስታት እጃቸውን ያላስገቡበት ጊዜ የለም። ኤርትራ የተባለች ሀገር እንድትፈጠር በማድረጉ ረገድ የቀድሞዎቹ የሱዳን ገዢዎች የነበራቸው አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ከቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ደርግ ጊዜ በዘለቁት በርካታ አመታት የሱዳን መንግስታት በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሲገቡ ቆይተዋል። ህወሃት በ17 አመታት የርስበርስ ጦርነት ወቅት ወልቃይትንና አካባቢውን በመቆጣጠር የመጀመሪያውን የውጭ ግንኙነት መስመር የከፈተው በኢትዮ-ሱዳን ድንበር በኩል ነበር። በወቅቱ የህወሃት አመራሮች ከውጭ ሃይሎች ትጥቅና ሎጂስቲክስ ያስገቡ የነበረው በሱዳን ድንበር በኩል እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያመለክታሉ። አሁን መንግስት የሆነው በፕሬዝዳንት ኢሳያስ የሚመራው የኤርትራ ተገንጣይ ሃይል ዋና አስተላላፊ የነበረችው ሱዳን ናት።
የሱዳን ወረራና የህወሃት አርሚ ሰባ ድጋፍ
ከዚህ ባለፈም ከዛሬ አምስት አመት በፊት የፌደራሉ መንግስት እና ህወሃት ወደ ፍልሚያ በገቡበት ወቅት የሱዳን መንግስት አጋጣሚውን በመጠቀም የኢትዮጵያን ግዛት በሃይል ወረረ። አልፋሽጋ የመሄረሻ መሬት በሱዳን እጅ የገባችው በዚያን ጊዜ ነበር። በወቅቱ ሱዳን እንዳሁኑ በጦርነት ውስጥ አልነበረችም። ከዚህ ባለፈም ጀነራል አልቡርሃን የህወሃት አርሚ ሰባ የተባለው ሃይል ዛሬም ድረስ በሱዳን ምድር ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስድ እንደዚሁም ለማጥቃት የሚመቸው መንደርደሪያ ቦታም እንዲያገኝ በማድረጉ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
የሱዳን ክፍፍልና የግብፅ ተጽዕኖ
አሁን ሱዳን በሁለት ሃይሎች ተከፍላለች ማለት ይቻላል፤ በጀነራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን እና በጀነራል መሃመድ አምዳጋሉ። ጀነራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን የግብጽ ጉዳይ አስፈጻሚ መሆናቸውን በግልጽ አሳይተዋል። ከናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን እና ግብጽን በብቸኝነት የምታዋስነው አገር ሱዳን ናት። ሱዳን በኢትዮጵያ እና ግብጽ መካከል የምትገኝ ሀገር ናት። ከአባይ የሚፈሰው ውሃ ግብጽ የሚደርሰው 100% የሱዳንን ግዛት አቋርጦ ነው። ስለዚህ በአባይ ጉዳይ ሁልጊዜም የራሷን ጥቅም ብቻ ማስጠበቅ የምትፈልገው ግብጽ ሱዳንን መጠቀሚያ ማድረጓ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ግብጽ የ86% የአባይ ውሃ ምንጭ የሆነችውን ኢትዮጵያ የውሃ ድርሻ ዜሮ በማድረግ 100% የአባይ ውሃ የተከፋፈለችው ከሱዳን ጋር ብቻ ነው።
የኢትዮ-ሱዳን ግንኙነት መሻሻልና የህዳሴው ግድብ ድጋፍ
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የተወሰነ የግንኙነት መሻሻል ውስጥ የገቡት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡመር አልበሽር እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በነበራቸው የግል ወዳጅነት ግንኙነት ነበር። የሁለቱ መሪዎች ወዳጅነት ወደ ሃገራዊ ግንኙነት ከፍ ብሎ ኢትዮጵያ ለሱዳን የኤሌክትሪክ ሃይል እስከማቅረብ ደርሳለች። የህዳሴው ግድብ ሲገነባም አልበሽር ከግብጽ አስተሳሰብ በማፈንገጥ በግልጽ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። በአባይ ጉዳይ ሱዳን ከእጄ ልትወጣ ነው ብላ የሰጋችው ግብጽ አልበሽር መወገድ አለባቸው የሚል ጽኑ አቋም ነበራት።
የአልበሽር ከስልጣን መወገድና የጄኔራሎቹ መምጣት
በመሃል አቶ መለስ ዜናዊም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አልበሽርም ህዝባዊ አመጽና ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በተቀላቀለበት የፖለቲካ ትርምስ ከስልጣን ተወገዱ። ይህን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎም አሁን ለሁለት ተከፍለው ሱዳንን እርስ በእርስ እያናወጧት ያሉት ጀነራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን እና ጀነራል መሃመድ አምዳጋሉ ወደ ፊት መጡ።
የግብፅና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ
ከሁለቱ ጀነራሎች መካከልም ጀነራል አል-ቡርሃን በምክር ቤቱ መሪነት የሃገሪቱን መሪ ሆነው ተሹመዋል። እሱም ከግብፅ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ስጋት ውስጥ ለመክተት የግብፅን አየር ሃይል ሱዳን ምድር ውስጥ አስገብቶ የጋራ የጦር ልምምድ እስከማካሄድ ደረሱ። ይህ የግብፅና ሱዳን የጦር ልምምድ "የናይል ንስሮች" የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህ የጋራ ጦር ልምምድ እንደተጠናቀቀ ብዙም ሳይቆይ በ2023 በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ተቀሰቀሰ። ግብጽ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋት፤ በቻለችው አቅም ሁሉ ጦርነቱን ለማስቆም ጣረች፤ ግን አልተሳካም።
ሱዳን በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ያደረሰችው ጉዳትና የደርግ ምላሽ
በተለይ በደርግ ዘመን ሱዳን የኢትዮጵያን የእርስ በርስ ጦርነት በማቀጣጠሏ ከባድ ኪሳራ አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በዘመነ ደርግ በእርስ በእርስ ጦርነት በምትናወጥበት ወቅት ሱዳን በዚሁ ጦርነት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፏን በመቀጠሏ የወቅቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምም "እሾህን በሾህ" በሚል የደቡብ ሱዳን ተገንጣይ አማጽያንን ማገዝ ጀመሩ። በኮሎኔል መንግስቱ ድጋፍ ዛሬ ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ተገንጥላ ራሷን የቻለች ሃገር ሆናለች። ይህ የሆነው የሱዳን አመራሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ እጃቸውን ባለማሳረፋቸው ነበር። በወቅቱ አለም በቀዝቃዛው ጦርነት ውስጥ የነበረችበት ወቅት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አገሪቱን ለመበታተን ቆርጠው የተነሱበት ወቅት ነበር። በዚህ ረገድ አረቦች፣ ኮሚኒስቶች፣ የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆኑት ሶማሊያ እና ሱዳን እንዲሁም የኤርትራ ታጣቂ ሃይሎች ዋነኛ የፖለቲካ ተዋናዮች ነበሩ። ግብጽ እና ሱዳን ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመነጠል በርካታ የቅንጅት ስራዎችን እየሰሩ ነበር። ሱዳን በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ እጇን ከማስገባት እንድትቆጠብ በደርግ መንግስት በኩል ብዙ ጥረቶች ሲደረጉ እንደነበር ሰነዶች ያመለክታሉ።
የደርግ የደቡብ ሱዳን ድጋፍና የአዲስ አበባ የሰላም ስምምነት
ይሁን እንጂ እነዚህ ጥረቶች ስኬትን ባለማስገኘታቸው ደርግ የደቡብ ታጣቂ ሃይሎችን ጦር በማደራጀት፣ በትጥቅ በመርዳት እና የስልጠና ቦታ በማዘጋጀት ከሱዳን የሚገነጠሉበትን ሁኔታ አመቻቸ። ታጣቂዎቹ ከኢትዮጵያ ምድር እየተነሱ ጥቃት እንዲሰነዝሩ የተመቻቸ ሁኔታ ተፈጠረ። ይህንንም የደርግ እርምጃ ተከትሎ ኢትዮጵያ በእርስ በእርስ ጦርነት ስትደማ ሱዳንም በሌላ አቅጣጫ ራሱ በለኮሰው እሳት መንደድ ጀመረች። በእርግጥ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት መቀጣጠል የጀመረው ሀገሪቱ ገና ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ እንደወጣች ነበር። በዘመነ ኃይለ ሥላሴ ሱዳን አደጋ ውስጥ እንዳትወድቅ ለማድረግ አጼ ኃይለ ሥላሴ የማሽማገል ሚና ነበራቸው። በሱዳን መንግስትና በወቅቱም ነፍጥ አንስቶ ሲፋለም በነበረው ታጣቂ ሃይል መካከል እርቅ እንዲወርድ በማድረጉ ረገድ አጼ ኃይለ ሥላሴ ቀላል የማይባል ስራን እንደሰሩ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በታሪክ የአዲስ አበባ የሰላም ስምምነት በመባል የሚታወቀው ስምምነት ሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች እጅ ለእጅ በማጨባበጥ ስኬት እንዲያገኝ ያደረጉት አፄ ኃይለ ሥላሴ ነበሩ።
የሱዳን ቀጣይ ጣልቃ ገብነትና የሸሪዓ ህግ መግለጫ
ሆኖም የሱዳን መንግስት ይህንን ሁሉ እውነት ታሳቢ ሳያደርግ በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ ገብቶ መፈትፈቱን ማቆም አልፈለገም። ይህ የመጀመሪያ የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በሰላም ከተጠናቀቀ በኋላ ሁለተኛው የእርስ በርስ ጦርነት የፈነዳው ፕሬዝዳንት ጃፋር ኒሜሪ በ1983 በመላ ሱዳን የሸሪዓ ህግ ተግባራዊ እንዲሆን አዋጅ ካወጁ በኋላ ነበር። በዚህ መልኩ ዳግም የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ለደርግ መንግስት አመቺ ሁኔታን ፈጠረ። ደርግም "እሾህን በሾህ" የሚለውን መርህ በመጠቀም የደቡብ ሱዳን ተገንጣዮች የትጥቅ ትግል ወደ ኋላ ሊቀለበስ ወደማይችልበት ደረጃ አደረሰው።
የኢህአዴግ መንግስትና የደቡብ ሱዳን ድጋፍ ማቆም
ይሁንና ደርግ የለኮሰውን የሱዳን ርስ በርስ ጦርነት የመጨረሻ ውጤት ሳይመለከት ከስልጣን ተወገደ። በእግሩ የተተካው የኢህአዴግ መንግስት በህወሃት በኩል የሱዳኑን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ደርግ ሲሰጥ የነበረውን የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲቆም አደረገ። በወቅቱ በጋምቤላ የነበረው የአማፅያኑ እንቅስቃሴ ሁሉ እንዲቆም ተደረገ። ይሁንና የደቡብ ሱዳን ተገንጣይ ሃይሎች የትጥቅ ትግል ወደ ኋላ የማይመለስበት ደረጃ ላይ ደርሶ ስለነበር በመጨረሻ ደቡብ ሱዳን ከሱዳን መገንጠሏ እውን ሆነ።
ሱዳንና የኤርትራ ነፃነት
ቀደም ብለን ለማሳየት እንደሞከርነው ሱዳን በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ በሰፊው እጇን ባታስገባ ኖሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እጅ ትወጣ ነበር ብሎ መናገር ያስቸግራል። የአረቦች የጦር መሳሪያ እርዳታ ወደ ኤርትራ ይገባ የነበረው በሱዳን በኩል ነበር። የህወሓት፣ የኢዲዩ፣ የጀብሃ እና የሻቢያ ዋነኛ ማዕከል እና የውጭ ግንኙነት መስመር ሱዳን ነበረች። በተለይ ለኤርትራ ታጣቂ ሃይሎች ፕሮፓጋንዳ እንዲያሰራጩ የሀገሪቱ ብሄራዊ ሬዲዮ ጣቢያ የነበረው ኦምዱርማን ሬዲዮ ሳይቀር ሰፊ የአየር ሰዓት ይሰጥ ነበር።
የሱዳን ኪሳራና የነዳጅ ሀብት መጥፋት
በድምሩ ይህ ሁሉ ሲታይ ኤርትራን ከኢትዮጵያ እጅ ፈልቅቆ በማውጣቱ ረገድ ሱዳን ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘች መገንዘብ ይቻላል። በውጤቱም ኢትዮጵያ የባህር ዳርቻዋን ከማጣት ባለፈ ወደ ደሃ አገርነት ተቀየረች። በሌላ በኩል ሱዳንም ብትሆን የእጇን በማግኘቷ ከፍተኛ ብሔራዊ ኪሳራ ደርሶባታል። ደቡብ ሱዳን ከመገንጠሏ ጋር በተያያዘ ሱዳን ከደረሱባት ጉዳቶች መካከል አንዱ በከፍተኛ ደረጃ የለማውን የነዳጅ ሀብትዋን ማጣቷ ነው። በሱዳን የነዳጅ ፍለጋ በስፋት መካሄድ የተጀመረው በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ነበር። ከበርካታ አመታት ጥረት በኋላም በ1990 ነዳጅ የማውጣቱ ስራ ተጀምሯል። ይህንንም ተከትሎ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ፍጹማዊ ለውጥን ማምጣት ጀምሮ ነበር። የነዳጅ ኤክስፖርት የሚያስገኘውን ገቢ ተከትሎ መሰረተ ልማቶች ተስፋፉ፤ የበርካታ ሱዳናውያን የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠንም አደገ። ሆኖም 80% የሚሆነው የነዳጅ ሀብት የመገንጠል ጥያቄን ባነሳችው ደቡብ ሱዳን ግዛት ስር መሆኑ ሲታሰብ ደግሞ በሱዳናውያን ዘንድ እያደር ስጋትን ማጫር ጀመረ። ከደቡብ ሱዳን ግዛቶች ተነስተው ከ1000 ኪሎ ሜትር በላይ አቋርጠው በፖርት ሱዳን በኩል ለአለም አቀፍ ገበያ ነዳጅ የሚያቀርቡት የነዳጅ ቱቦዎች የሱዳንን ኢኮኖሚ እንዲመነደግ ቢያደርጉትም በሂደት ግን ተስፋ የማሸሽ ሄደ።
የሱዳን ፖለቲካ አመራሮች ስህተትና የወደፊት ዕጣ
ደቡብ ሱዳን ስትገነጠል 80% የነዳጅ ሀብት በደቡብ ሱዳን ግዛት ስር መጠቃለሉ ለበርካታ ሱዳናውያን የእግር እሳት ቢሆንም የዘሩትን ማጨድ ግን ግድ ሆነባቸው። የሱዳን ፖለቲካ አመራሮች በተለይም የግብጽ አላማ ማስፈጸሚያ በመሆን በተጠነሰሱት ሴራ ኢትዮጵያ ወደ ኋላ ስትቀር እነሱም ሰፊ ግዛታቸውን ከማጣት ባለፈ የነዳጅ ሀብታቸውን አጡ። ለሱዳን ከግብጽ ይልቅ በብዙ መልኩ የምትቀርበው ኢትዮጵያ ነበረች። ግን ደግሞ የሱዳን መሪዎች ሁልጊዜም ግብጽ ስር በመሸጎጥ ኢትዮጵያን በብዙ መልኩ ሲያጠቁ ይታያሉ። ይህ ታሪኩን ልጫ አድርጎ በመዘገብ ያስቀመጠ እውነታ ነው። አሁን ደግሞ ዘመን ቆጥሮ አገሪቱ ልትወጣው በማትችለው ሌላ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እየማሰነች ትገኛለች።

