0:04 እሺ ተመልካቾች እንዴት ናችሁ? ይህ የኢኮኖሚ ጉዳይ እያልሳን የምናወራበት የዩትዩብ ቻናል ነው። እኔ ዋሲው በላይ ነኝ ቻናሉ ላይክ ሰብስክራይብ እንድታደርጉ እጋብዛችኋለሁ ብዙ ሰዎች የዚህን ያህል ብር አለኝ ምን ላድርግበት ወይም ደግሞ ምን ባደርግበት የተሻለ ውጤታማ ሊሆን ይችላል የሚል ጥያቄ አላቸው እናንተም ሊኖራችሁ ይችላል እኔም አለኝ አንዳንዶች በየመጠሩ በብዙ ሚሊየን ያላቸው አሉ ደግሞ ጥቂት የሆነ ብር ያላቸው አሉ ግን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለመወሰን የሚቸገሩ ሰዎች አሉ። ለዚህ ጉዳይ ትክክለኛ መልስ ለመስጠት ትንሽ ሊያስቸግር ይችላል ግን አንድ ስድስት አማራጮችን ላቅርብላችሁ
0:51 ፈልጌያለሁ። የኢንቨስትመንት አይነቶች ሳይሆኑ ነገር ግን ብር የያዙ ሰዎች የብራቸው ዋጋ እንዳይዳከብባቸው ምን አይነት ውሳኔ መወሰን ይችላሉ የሚል አንድ ስድስት አማራጮች አቀርብላችኋለው ሁሉም ፖሲብል እንኳን ባይሆኑ ግን ኢምፖሲብል አይደሉም። ግን ሁለት ነገሮችን ከግምት መጀመሪያ እንክተት አንደኛው የዋጋ ንረት አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ 13 ከመቶ ነው ሚባለው 15 ከመቶ ሆኖ ለአንድ አመት ቢቆይ የሚለውን ከግምት ከተን ነው ምናወራው። ሁለተኛውን ደግሞ ገንዘቡ በአንድ አመት ውስጥ ያለውን ለመለካት የሚል ታሳቢ ታደርጉልኛላችሁ ለምሳሌ 1 ሚሊየን ብር ካለው ሰው እንጀምር ለምሳሌ እንዲመች ነው ሙሉ ቁጥር የምናደርገው እናንተ 10ሺ ብርም 20 ሺ ብርም
1:38 ያላችሁ ሰዎች ምናልባት ወደ ራሳችሁ ኮንቴክስት ልትገለብጡት ትችላላችሁ የመጀመሪያው ጉዳይ ብሩ በሰውዬው እጅ ቢቀመጥ ብለን ነው የምናወራው ሌላ እኮ ምንም ምርጫ የለም ለምሳሌ አንድ ሚሊየን ብር እቤቱ ያለው ሰው እቤቴ ከማስቀምጠው ብሎ ነው የሚጀምረው ስለዚህ እቤት ማስቀመጥ እና አለማስቀመጥ ችግርም ትርፍም የሚሆነው ብሩ ካለው የመግዛት አቅም ጋር ተነስቶ ነው። ስለዚህ የዋጋነቱ 15 ከመቶ ነው የምንል ከሆነ አንድ ሰው አንድ ሚሊየን ብርን ቤት ውስጥ ለአንድ አመት ቢያስቀምጠው በቁጥር 1 ሚሊየን ብር ነው የሚሆነው። በቁጥር ደረጃ አንድ ሚሊየኑ ሊቀደድ አይችልም 1 ሚሊየን አለው። በመግዛት አቅም ግን በ15 ከቶ
2:24 ይቀንሳል ምክንያቱም የዋጋ ድ 15 ከመቶ ስለሆነ ምን ማለት ነው ዘንድሮ 100 ብር የሚገዛውን እቃ የሚቀጥለው አመት እሱኑ እቃ ለመግዛት አንድ መቶ አስራ አምስት ብር ያስፈልገዋል ወይም ደግሞ ተጨማሪ 15 ይጠበቅበታል ማለት ነው ስለዚህ የመግዛት አቅሙ በ15 ከመቶ ስለሚዳከም እጃችን ላይ ያለ ብሩ 1 ሚሊዮን ብሩ እጃችን ላይ ያለ የሚቀጥለው አመት 815 ሺህ ብር ነው የሚሆነው። በ150 ሺህ ብር 850 ሺህ ብር ነው የሚሆነው ይቅርታ በ150ሺ ብር የመግዛት አቅሞ ይዳከማል ማለት ነው። ወይም ዘንድሮ አንድ ሚሊዮን ብር ይገዛው የነበረውን የሚቀጥለው አመት ለመግዛት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር መጨመር አለብን ማለት ነው። ስለዚህ ብርን ቤት ውስጥ ማረግ ከስርአት ነው
3:11 የመጨረሻው ሌቭል ነው እንደማለት ነው። ሁለተኛው እሺ እጄ ላይ ማስቀመጥ የለብኝም ዋጋ እየበላብኝ ከሆነ ብሬን በባንክ ቤት ባስቀምጠው ደግሞ የሚለው ቀጥሎ ያለው ምርጫ ደግሞ ይኖራል። መርሳት የሌለባችሁ ባንክ ቤት ባስቀምጠው ተብሎ ሰዎች የቁጠ አይነቶች ይለያያሉ ከባንክ ባንክ የተወሰነ በጣም የተወሰነ ምክንያቱም የቁጠባ ወለድን የሚወሰነው ብሄራዊ ባንክ ስለሆነ ከአንዱ ባንክ አንዱ ባንክ በዋናነት የሚለያይ አይደለም ግን የሴቶች የጻናት የሀሳውንት እያሉ የትንሽ ፐርሰን ልዩነት ትመለከታላችሁ ግን የናሽናል ዲፖዚ ኢንተረስት ሬዝ ግን 7 ከመቶ ነው ስለዚህ ባንክብ አስቀምጠውና 7 ከመቶ ቢታሰብ ለአንድ አመት ገንዘቡ ቢቀመጥ
3:57 ቢባል ምናልባት የአንድ ሚሊየን ሰባት ከመቶ ቢሰራ ኢንተረስት ሬት እስኪ እስኪታሰብበት ወለድ እስኪታሰበት ማለቴ ነው ወለድ እስኪታሰብበት ሰባ ብር ይሆናል በቁጥር ደረጃ ግን ወለድ የሚታሰብበት ነው ይሄ ገንዘብ ገቢ ስለሆነ ከወለድ የተገኘ ገቢ የገቢ ግብር አለበት የገቢ ግብር ብትቀንሱ መቀነሱ አይቀርም ከ70ሺ ብሩም ይቀንሳል ማለት ነው በአንድ አመት ተቀምጦ ዋጋ ንረቱ በ150 ሺህ ብር የመግዛት አቅሙን ገንዘቡን ቀንሶታል ዋጋረቱ ገበያው ላይ ስላለ ማለት ነው ባንኩ ምናልባት 60 ሺህ ብር ከሆነ ለዚህ ገንዘብ የሚያስበው በአመት የገቢ ግብሩን
4:44 ቀንሶ እ 70 እና 80 ሺ ብር ነው የክስረት መጠኑ የሚቀንሰው ይከስር የነበረው 150 ሺ ብር ይከስር ነበር ይሄ ሰው የገንዘብ የመግዛ መግዛት አቅሙ በጣም በ15 ከ100 ስለሚዳከም ነገር ግን ባንኩ 60 ሺህ ብር እንኳን ቢያግዘው ክስረቱ ከ150 ሺህ ብር ወደ 90 ሺ ብር ነው ዝቀሉ። ከክስረት አልዳነም ማለት ነው። ከዋጋ ዋጋ ንረቱ ከባንክ ወለድ በታች እስከሆነ ድረስ ሰው መክሰሩ አይቀርም። ነገር ግን ምናልባት ቁጠባ የጊዜ ገደብ ቁጠባ ላይ ቢያስቀምጥና የጊዜ ገደብ ቁጠባው ከ 15 ከመቶ በላይ ከሆነ የገቢ ግብሩም ተቀንሶ 15 ከመቶ እንኳን አማካኝ እንኳን ቢሆን ከስራት ዜሮ ሊሆንለት ይችላል ቁጠባ ባህሪው ይለያያል ለምሳሌ
5:30 የጊዜ ገደብ ማለት ነው አንድ አመት ሙሉ ያቺን ገንዘብ አልነካትም ብሎ ተዋውሎ ቢያስቀምጠው ማለት ነው እሱም ከ15 ከመቶ በላይ መሆን አለበት የገቢ ግብሩ ሲቀነስ 15 ከመቶ ዋጋነት የሚጨምርበትን እንዲያቻችል ስለዚህ ይህ ሰው አላተረፍም አልከሰረም ዋጋ ንረቱን ተከትዬ ሄጃለሁ ሊል ይችላል። ገንዘብን ባንክ ማስቀመጥ እቤት ከማስቀመጥ የተሻለ ሶስተኛው አሁን ስለ ጥሬ ገንዘብ ስለሆነ ሰውዬው እጅ ላይ ያለው አክሲዮን ቢገዛበት ብለን እናስብ ምናልባት የግንጃቤ ሰነድም ሊሆን ይችላል አክሲዮንም ሊሆን ይችላል ቦንድም ሊሆን ይችላል የሚገዛው እነዚህ ሰነዶች በአንድ አመት ውስጥ የሚገዙ ሰነዶች ከሆኑና የሚገኝባቸው ትርፍ ይሄም በአክሲዮንም በቦንድም የሚገኝ ትርፍ ገቢ
6:20 ስለሆነ ግብር የሚጣልበት ነው የገቢ ግብር ያለበት ከ7 ከቶ በላይ ከሆነ የገቢ ግብሩ ተቀንሶ የሚገኘው የትርፍ መጠን ከ7 ከቶ በላይ ከሆነ እቤት ከማስቀመጥም የተሻለ ነው ባንክ ከማስቀመጥም የተሻለ ነው። ደግሞ ፍጹም በቤት ከማስቀመጥ ደሞ የተሻለ ነው። እና ግን ጥሩ የሆኑ አክሲዮኖችን ከገዛ ነው አዋጪ የሚባሉ አክሲዮኖችን በጥናት ለይቶ ከገዛ ነው። ምናልባት የመጀመሪያ አመት ላይ አንዳንድ አክሲዮኖች ትርፍ ላይኖራቸው ይችላል። ነገር ግን አትራፊ የሚባሉ አሉ አክቲቭ የሆኑ የባንኮችን የሚገዛ ከሆነ የመጀመሪያ አመት ላይ እንኳን ባያገኝ ሁለተኛ አመት ሶስተኛ አመት ላይ አሁን ለመግዛት ያወጣውን ወጪ ሊያካክስ ይችላል ለምሳሌ አንድ ሚሊየኑን እ በአንድ ሚሊየኑ የ800 ወይም ደግሞ የዘጠኝ መቶ ሺ
7:08 ብር አክሲዮን ቢገዛበት ምክንያቱም ስራ ላይ ያለ ውጤታማ የሆነ አክሲዮን በዛ ዋጋ ላይ ሊኖር ስለሚችል ለምሳሌ ስራ ላይ ያሉ ባንኮች ከሆኑ የመቶ ብሩን አክሲዮን በ120 በ130 ብር ነው የሚገዛው ነው። ስለዚህ አንድ ሚሊየኑ የ800 ምናምን ሺ ወይ 900 ሺህ ብር አክሲዮን ቢገዛለት የሚገኘው ትርፍ ሁለተኛ አመት ሶስተኛ አመት ላይ አሁን ያወጣውን ወጪ ል በብዙ መጠን ሊያካክስለት ይችላል። እንደተገዛ የመጀመሪያው አመት ላይ ትርፍ ይገኛል ብሎ የሚታሰብ አይደለም። ስለዚህ የመጀመሪያው አመት ላይ ጥሩ ባንክ ጥሩ ሰነድ ካገኘሁና ሶስተኛ አመት ላይ መጀመሪያ ላይ የገዛሁትን ኢንቨስትመንት ያሻሽልኛል ብሎ ከታሰበ ውጤታማ ሊሆን ይችላል ነገር ግን የገዛው ሰነድ ቶሎ ትርፍ
7:56 የማይሰጥም ሆኖ ደሞ የሚሰጠውም ትርፍ በጣም ዝቅተኛ ከሆነ የገቢ ግብር ተቀንሶለት ከ70 ከመቶ በታች ከሆነ ከባንክ ማስቀመጥ የሚሻል አይደለም ምናልባት ሰነዱ እንደ እንደ ማስያዣ ሚጠቀም ካልሆነ በስተቀር ማለት ነው ስለዚህ ከሰባት ከመቶ በታች ከሆነ ከቤት ከማስቀመጥ ይሻላል ነገር ግን ከባንክ ከማስቀመጥ ዝቅተኛ ነው ከሰባት ከመቶ በላይ ከሆነ ሆነ ግን ከባንክም እቤትም ከማስቀመጥ የተሻለ ሊሆን ይችላል። ምርጫዎቹን ማወቅ ነው ያለባችሁ ውሳኔው የናንተ ጉዳይ ሊሆን ይችላል አራተኛው ደግሞ ኢንቨስት ማድረግ የሚችል ቢሆን የሰው 1 ሚሊየን ብር ያለው ሰው ኢንቨስት ሚያረጋቸው የአንድ ሚሊየን ቢዝነሶች ቢኖሩ ወይ በራሱ በነጠላ ወይም ከሰዎች ጋር በጋራ የሚሰራው ቢዝነስ ንግድም ሊሆን ይችላል ምርት ማምረትም ሊሆን ይችላል
8:43 አገልግሎት መስጠትም ሊሆን ይችላል በነጠላም በጋራም የተጠና ኢንቨስትመንት ላይ አዋጪ ተብለው የታሰቡ የተጠኑ ኢንቨስትመንቶች ላይ ሚንቀሳቀስ ከሆነ ትጋት ካላቸው በቂ ትጋት ካላቸው ከዋጋት በላይ ገቢ ሊያገኙበት ይችላሉ ምናልባት ቋሚ ንብረትም ሊያፈሩበት ይችላሉ ለራሳቸው የሆነ ደሞ ስራ ሊፈጥሩበትም ይችላሉ ሁሉም ጉዳይ አንዳንዴ በገንዘብ ብቻ አይተመንም ሰሎ እራሱ ስራ ከፈጠረ ስራ አለኝ የሚለው ስሜትም በራሱ ጥሩ ስሜት ይሰጣል ግን ኢንቨስትመንት ከባድ ውሳኔ ነው በጣም ጥንቃቄ ሚፈልግነው ትጋት የሚፈልግነው ያልተጠና ኢንቨስትመንት ከሆነ መቆጠብ እና ቦንድ መግዛት ይችላል። ምክንያቱም ከስርዓት ሊመጣ ይችላል ቢዝነስ ጀምሬ ከስር ዘጋውት የሚሉ ሰዎች አሉ።
9:31 ከመዝጋት ወይ ደግሞ ከመክሰር ያለውንም ብር ከመክሰር ባንክ አስቀምጦ የዋጋ ንቱ ትንሽ እየቀለለለት ቢቆይ ይሻላል እጁ ላይም ይዞ 15 ከመቶ ብቻ በየአመቱ ቢከስር ይሻላል ለምሳሌ አንድ ሚሊየን ብር ኢንቨስትመንት ጀምሮ 500,000 ብርን ከስሮ 500,000 ብር ብቻ የቀረው ሰው ኦልሞስት ግማሹን ከሰረኩ እቤቱ ቢያስቀምጠው የሚከስረው 15 ከመቶ ብቻ ነው። ባንክ ቢያስቀምጠው የሚከስረው ስምንት ከመቶ ብቻ ነው። 7 ከመቶን ባንኩ ስለሚያስብለት ማለት ነው። ስለዚህ ያልተጠና ከሆነ መቆጠብ እና በወንድ መግዛት ነው ሊያዋጣ የሚችለው። ግን የተጠና እና ትጋቱን ጠብቆ መስራት የሚቻል ከሆነ ኢንቨስትመንት ከዋጋት በላይ ነው ቋሚ ንብረት ሊፈራበት የሚችል ነው። ደግሞ ለተራ ስራ መፍጠር የሚቻል ነው ወደፊትም ብራንድ ማሳደግ የሚቻልበት ነው። አራተኛው እሱ
10:16 ነው። አምስተኛው ምናልባት ቋሚ ንብረት መግዛት የሚችል ከሆነ ገንዘቡ ቋሚ ንብረት ላይ ቢያውለው ብለን ደግሞ እናስብ ምናልባት ገንዘቡ የሚችል ከሆነ ቤት የገዛ ሰው እጅግ በጣም ጥሩ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ቤት በአንድ አመት ውስጥ ራሱን በምን ያህል ፐርሰንት እንደሚጨምር የምትለው በብዙ ፐርሰንት የሚጨምር ነው። መሬት በብዙ ፐርሰንት የገበያ ዋጋው ቫልዩ የሚጨምር ነው። አሁን የፖሊሲ ልዩነት ከሌለ በስተቀር መኪናም አገለገለ ተብሎ ዋጋው የሚቀንስበት አይደለም የኢትዮጵያ አገልግሎም ዋጋው የማይቀንስበት ነው። ዲፕሪሺን ቫልዩ እንኳን ከፍተኛ ሆኖ ነገር ግን ዋጋው የሚጨምር ንብረቶች ናቸው እነዚህ። ስለዚህ እነዚህን ገዝቶ በአመቱ እንኳን የሚሸጥ ሰው ፕሮፊት ማርጅኑ ከዋጋ ንረት እጥፍ እጥፍ በላይ ነው
11:03 የሚሆነው። መግዛት የሚችል ከሆነ ማለት ነው። ነገር ግን ቤትም መግዛት የሚችል፣ መሬትም መግዛት የማይችል፣ መኪናም መግዛት የማይችል ገንዘብ ከሆነ በጣም የተለመዱ ደግሞ ጌጣጌጦች ሊሆኑ ይችላሉ። ይሄኛውንም ምርጫ ብዙዎች ይጠቀሙታል። ወርቅ ገዝቶ የሚያስቀምጡት ያሉት ሰዎች አሉ። ወርቅ መግዛት ምናልባት ቤት ከማስቀመጥ ባንክ ከማስቀመጥ ሊሻል ሊሻል የሚችልበት አማራጮች ይኖራሉ ነገር ግን እንደዚህ አይነት ወርቅ ምናምን የሚባሉ ንብረቶች አሮጌ የእቃነት ባህሪ ስላላቸው እና ደግሞ ዋጋቸው ላይ እርግጠኛ መሆን የሚቻልበት አይደለም። ለምሳሌ አሁን በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የወርቅ ዋጋ እየጨመረ ነው በግራ ብሄራዊ ባንክም መነቃቃት አለው ኤክስፖርቱም እያደገ ስለሆነ ከሱ ከሱ ጋር ተያይዞ የማደግ አለው ግን የሆነ ሰው ወርቅ ገዝቶ የሚቀጥል በቀጥሎ አመት ልሽት ካለ የአሮጌ የእቃነት
11:49 ባህሪ ስላለ እንደ በፊቱ የቋሚ ንብረት አይነት ባህሪ አለው ብሎ ለመናገር ትንሽ ያስቸግራል ዲፕሪሺን ዲፕሪሺየት ያደርጋል ወርቅ አምና የገዛሁት ወርቅ ቢባል ዘንድሮ ላይ ከአምናው በጣም በብዙ የመጨመር አይነት ልምድ አለው ብሎ ለመናገር ትንሽ ያስቸግራል ግን ከሆነ ቤት ከማስቀመጥ እና ባንክ ከማስቀመጥ አንጻር ምናልባት የዋጋነት ቫልዩ ድረስ ሊያዛልቅ የሚችል ነው። አንዳንዶች ምናልባት ገንዘቡን አሁን ከሚይዘው ሶፋ ልግዛበት፣ ቲቪ ልግዛበት ንብረት የቤት ውስጥ እቃ ልግዛበት የሚሉ ሰዎች አሉ። ምናልባት ወደፊት የሚጨምር ዋጋ ስለሆነ እነዚህን ንብረት ገዝቼ ሊያዝ ለሚለው ምርጫ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ እቃዎች ዲፕሪሺየት የሚያደርጉ ናቸው። ለምሳሌ ቴሌቪዥን ከሆነ ሞዴሎች የሚያልፍባቸው ናቸው
12:36 ሶፋም ከሆነ ሰዎች የሚጠቀሙበት ዲፕሪሺ የሚያደርግ ስለሆነ የሚቀጥለው አመት ምናልባት ከዋጋ ንራት በላይ ይችላል። ግን አይ ዝም ብዬ ገንዘቡን ከሚይዞ እና እያየሁት ከሚዳከምበት ቲቪ ገዝቼ እየተጠቀምኩበትም ነገር ግን 10 ከመቶ እንኳን ዲፕሪሺየት ብቻ አድርጎ ብሸጠው የሚል ምርጫ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ ሊያዋጣቸው ይችላል። ዝምብሎ መያዝ 15 ከመቶ እያዳከመ ነው ስለዚህ እኔ ቴሌቪዥን ገዝቼበት አንድ አመት ተጠቅሜበት የሚቀጥለው አመት በአስር ከመቶ ብቻ ዲፕሪሺ አድርጎ ብሸጠው ካሉ ከስረታቸውም ቢያንስ ወደ አምስት ፐርሰንት ዝቅ ሊያደርጉ ይችላሉ ባንክ ከማስቀምጠው ብለው ካሉ ደግሞ ዲፕሪሺየት የምታደርገውን ያህል መጠን መጠበቅ ሊሉ ይችላሉ። እሱም የድርድር ጎሼት የማድረግ የመሸጥ አቅም በራሱ የሚወሰን ስለሆነ ማለት
13:22 ነው። ሌሎች ንብረት መግዛት የሚችሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ምናልባት የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች የሚገዙ ሊኖሩ ይችላሉ። አሁን በዋጋ ንረት ደረጃ ምግብ ነክ ያሉ ዋጋቸው በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። ከባለፈው ጁን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሲታይ መቀነስ እያሳየሁ ያልሆኑት የምግብ ነክ ያልሆኑት ቁሳቁሶች ናቸው። የኮንስትራክሽን እቃዎች ሌሎቹ። ምናምን ምናልባት የኮንስትራክሽን እቃዎችን ገዝቶ ስቶክ የሚያደርጉ ሰዎች ከሆኑ ወጪዎቻቸው ሊሸፍኑ ይችላሉ ከዋጋት በላይ ሊያገኙ ይችላሉ። ንብረቱም ይወስነዋል የሚገዛውም ንብረት ይወስነዋል እንደየ ገንዘብ መጠናችሁ ማለቴ ነው። ስድስተኛው የውጭ ምንዛሬ ኢንቨስትመንት አሁን ይሄ የሚፈቀር ነው የማይፈቀር ነው የሚለው ጉዳይ እራሱን የቻለ ጉዳይ ነው ግን ኢምፖሲል ብለን ምናስበው አይደለም። ሰዎች እዚህ ኢንቨስትመንት
14:10 ውስጥ የሉም ብሎ ምንናገረው አይደለም አቁን እንነጋገር ከሆነ ከተባለ የውጭ ምንዛሬ አካውንት ኖሯቸው እንዲይዙ የሚፈቅድላቸው ሰዎች ምናልባት የዲያስፖራ አካውንት መክፈት የሚችሉ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዳላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ይላል የብሄራዊ ባንክ መምሪያ ግን ሁሉም ሰዎች የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ ውስጥ ያሉት በዚህ ጉዳይ ነው ብሎ መናገር አይቻልም ኢምፖሲብል ነው የሚባል አይደለም ነገር ግን ኦፖርቹኒቲው ያላቸው ቻንሱ ያላቸው ቢዝነሱን የሚሰሩ ሰዎች እና የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚችሉ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥም ሊሆኑ ይችላሉ ከኢትዮጵያ ውጪም ሆነው ግን ኢንቨስትመንቱ ላይ ያሉ ሰዎች ከተለመ ከተመለከተ ፕሮግሬሲቭ የሚባለው ኢንቨስትመንት ታይፕ ነው የውጭ ምንዛሬ ምን ማለት ነው በየቀኑ ዋጋው ለውጥ ያለው ለምሳሌ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ የአንድ የአሜሪካ ዶላር እንግዲ
15:00 በትልቁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንኳን ብንመለከት ከ124 ወደ 131 ብር ነው በሰባት ብር ልዩነት አለው አንድ አሜሪካዊ ዶላር የዛሬ አምስት ወር በ124 ብር ነበር ይገዛ የነበረው አሁን በ131 ብር ነው የሚገዛው። የሰባት ብር ለውጥ አለው በአምስት ወራት ውስጥ ማለት ነው። ምን ማለት ነው? የዛሬ አምስት ወር አንድ ሚሊየን ብር የነበረው ሰው በ124 ብር ዋጋ የውጭ ምንዛሬ ኖሮት ቢሆን ኖሮ ብለን ብናስብ ወደ ስምንት ስልሳ አራት ብር ዶላር ነበረው ማለት ነው። አንድ ሚሊየኑ ወደ ስምንት ስልሳ አራት ዶላር ኮንቨርስ ይደረግ ነበር። ያቺን 864 ዶላር ይዟል። አሁን 131 ብር ሲገባ ይሄን የውጭ ምንዛሬ ቢመነዝረው በመቶ 131 ብር ስለ ህጋዊ የብንዛሪ ተመኑ ነው
15:46 የምናወራው ስልዚህ ስንት ሊያገኝ ይችላል ማለት ነው ወደ 56000 ብር ልዩነት አለው ልዩነት አለው ማለት ነው በአምስት ወራቶች ውስጥ አንድ ሚሊዮኑ 56ሺ ብር ልዩነት አለው በፖዘቲቭ ማለት ነው ቅድም የገቢ ግብር እንኳን ተከፍሎበት ባንኩ አንድ አመት በሙሉ 1 ሚሊየኑን ቢይዘው ስንት ብር ያገኛል ነው ያለው 70,000 ብር እንኳን ቢሆን የገቢ ግብር ቢቀነስለት ምናልባት 60,000 ብር ቢሆን እንኳን ብለን ብለን እያሰብን ነበር። ይሄ በ5 ወር ውስጥ 56,000 ብር እያለን ነው። ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ቶሎ ቶሎ እራሱን እየለወጠ እያደገ እያደገ ነው የመጣው። የጨረታ ዋጋ እንኳን በአማካኝ ከ50 ሳንቲም በላይ ነው የሚጨምረው በየስራ አምስት ቀኑ በብሔራዊ ባንግ ጨረታ። እና ይሄ ቀላል አክሰሰቢል ነው ማለቴ አይደለም። ግን
16:32 ኢምፖሲብል ነው ብሎ መናገር አይቻልም። ፎሬክስ ቢዝነስ ውስጥ ያሉ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል። ለምሳሌ ለምሳሌ በሶሻል ሚዲያ እንኳን ገንዘብ የሚያገኙ ሰዎች ባንኮቻቸውን ሊለውጡ ይችላሉ። ለምሳሌ 130 ብር በሚመነዙሩ ሰዎች ደንበኛ መሆን እና 132 ብር የሚመዝሩ ባንኮች ደንበኛ መሆን ሁለቱ ይለያል። የ1 አንድ የአሜሪካ ዶላር በ131 የሚመዙሩ ባንኮችን ትቶ 132 ብር የሚመዙርበት ጋር ከሄደ አንድ ባለሃብትም አንድም የውጭ ምንዛሬ ያለው ሰው ልዩነት ፈጠረ ማለት ነው በአንድ ዶላር አንድ ብር እየለወጠ ነው ከባንክ ባንክም ልዩነት አለፎ ቢዝነስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደግሞ ከሀገር አገር ባንግላዲስ ጥሩ ከሆነ ምናልባት ከብራዚል ይሆናል የብራዚል ጥሩ ከሆነ ከኢንዲያ ሊያደርጉ ይችላሉ። እንደዚህ አይነት የፎሪክ ቢዝነሶች እንዳሉ
17:17 ይታወቃል። ደሞ ገንዘቦቻቸውም በዋጋረትም በተለያየ ምክንያትም ወደ ውጪ ምንዛሬ ለውጠው ደግሞ ስፔክሌት የሚያደርጉ ሰዎች የሉም ብለን አንከራከርንም። እነዚህ ምርጫዎች ይኖራሉ ሰዎች እጅ ውስጥ በየብሩ መጠን እናንተ ልትመለከቱ ትችላላችሁ እኔ በደረጃ አስቀምጥ ብትሉኝ በጥናት ከሆነ በጣም በጥንካሬ በተጠና መልኩ ቢዝነስ መስራት የሚሹ ሰዎች ከሆኑ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እመክራለው ኢንቨስትመንት የንግድ ኢንቨስትመንት ገዝቶ የመሸጥ አምርቶ የመሸጥ አገልግሎት የማቅረብ ኢንቨስትመንት ውስጥ በጥንካሬ መግባት የሚችሉ ኮሚትመንቱ ካላቸው በጥናት አዋጭ ቢዝነስ የለዩ ሰዎች ከሆኑ እዚህ ቢዝነስ ውስጥ ቢገቡ አሁንም አትራፊ ለረጅም ጊዜ አትራፊ የሆነ ቢዝነስ ግን ከባድ ኮሚትመንት የሚጠይቅ ጥናት የሚጠይቅ ቢዝነስ
18:04 እንደሆነ አምናለሁ እኔም ሁለተኛው ከተቻለ ቋሚ ንብረት ላይ ኢንቨስት ማድረግ የሚችሉ ሰዎች ለምሳሌ ብሩን ብቻ ከሚይዙ ለምሳሌ ቤት መግዛት የሚችል ገንዘብ ከሆነ ቤት መግዛት የሚችሉ ሰዎች መሬት መግዛት የሚችሉ ሰዎች መሬት መግዛት መሬታቸው ላይ ግንባታ ሊያከናውኑ ይችላሉ። ቤት ሰርተው ሬንት ሊያደርጉ ይችላሉ። ቤት ሰርተው ሬንት እያደረጉ ያከራየሁ የሚያገኙት ገቢ አለ ደግሞ ቤቱን ሲሸጡ ደግሞ የሚያገኙት ገቢ በእርግጠኝነት ከዋጋ ንረት በጣም ብዙ ፐርሰንታይ እጥፍ ነው። ቀላል ነው። ቀላል የዛኛውን ቅድም ቅድም የጠቀስኩትን የመጀመሪያው አይነት ኢንቨስትመንት ነው ያለው የሚያደክም አይደለም። ሰዎች ቤት ገዝቶ ቁጭ ባይደርጉት ከፍተኛ ጥረት ውስጥ የሚገቡበት አይደለም በቃ ቤቱን ገዞ አለቀ የውል ጉዳይ ጨረሱ አለቀ በቃ ተቀመጠ ታይም ቫልዩ ኦፍኔ አለ
18:50 የሚቀጥለው አመት ላይ ዋጋው ይጨምራል ሁለተኛው ሶስተኛው እንግዲህ የፎርክስ ቢዝነስ መጥፎ የሚባል ቢዝነስ አይደለም ደሞ በጣም ቀላል ነው ለምሳሌ ስፔኩሌት አድርገው ዋጋው ሲጨምርላቸው የሚሸጡ ሰዎች ከፍተኛ ጥረት ጥረት ያደርጋሉ ብሎ የሚናገር አይደለም። የሰው ሃይል መምራት አይጠበቅባቸውም ማምረት አይጠበቅባቸውም መሸጥ አይጠ ማጓጓዝ የሚባል ጉዳይ የለም ህጋዊነቱን ብቻ ጠብቆ የፎሪክስት ቢዝነስ ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ገዝቶ እንደመሸጥ ነው። ስለዚህ ቀላል የሚባል ኢንቨስትመንት የለም ግን ከጠራታችሁ ጋር መሰረት ያደረገ ነው የሚለውን እንድትገነዘቡ ነው እንደዚህ አይነት ሃሳብ ያለበት የዩቱብ ቪዲዮ የዛሬ ሁለት አመት አይንክ ሰርቼ ነበረ ግን አሁንም በጣም ቦሰቦች ስለሚጠይቁ ይሄን መረጃ ምናልባት
19:37 የሚጠቅማችሁ ከሆነ የሆነ ለናንተ ለማቅረብ ነው እኔ በሚሊየን ምሳሌ እያቀረብኩ ነው እንጂ 10,000 ብርም ያላችሁ ሰዎች በራሳችሁ ኮንቴክስት ይሄን ድራይቭ ልታደርጉት ትችላላችሁ። ስለዚህ ምናልባትም አንዳንድ ሰዎች ብማረበትስ ይላሉ ቢማሩበትም ኦፍኮርስ መጥፎ አይደለም። ዝምብሎ ብር ሰው ቤቱ ከሚያስቀምጥ ትምህርት ለመማር ቢወስን መጥፎ አይደለም። ግን ትምህርቱ ለምን እንደሚጠቅመው ግን ማወቅ አለበት ለስራ ነው ወይ? ለቢዝነሱ ነው ወይ? ወይስ ፐርሰናል ቫልዩን ለማሳደግ ነው የሚማረው? አንዳንድ ትምህርት አለ ተምረነው መተን ሼልፍ ውስጥ አስቀምጠነው ወደ ህይወታችን አንዳንድ ኮንፈርት የማይደረጉ ትምህርቶች አሉ ለሰነድ ብቻ ብለን የምንማራቸው እነሱ ማለት ዋጋ ያላቸው አይደለም ለነሱት ኢንቨስትመት ይመከራል ግን ኢንቨስት ያደረገ ሰው ከሆነ በማንበብ ውስጥ ራሱን አፕግሬድ ለማረግ አዳዲስ ውሳኔዎች የመወሰን አቅም እንዲያዳብር ትምህርቱን
20:25 ከጨረሰ በኋላ ለራሱ ፕሮፌሽናሊዝም እንዲያሳድግ የሚረዳው ከሆነ አሁን ለትምህርት ያወጣው ወጪ ይከፍላዋል ሰውዬው ነገር ግን ይሄ ሰነዱን ይዤ ልምጣ ብቻ ያለ ሰው ሰነዱ ብቻ ሊከፍለው አይችልም ለሰው ስለዚህ ኢንቨስትመንቱ ሌላ ኢንቨስትመንት እንዲሆን ነው ምንመክረው ስለዚህ እነዚህን አማራጮች እንድትመለከቱ ነው ተመልካቾች ማንኛውም ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ እዚህ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቪው ቴሌግራም ፌስቡክ ላይ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ ለነበረን ቆይታ በሙሉ ከልብ ከልብ አመሰግናለሁ መልካም