0:01 [ሙዚቃ] ቦርዳ የአፋር ህዝብ በቀይ ባህር አካባቢ ባለው ስትራቴጂካዊ አሰፋፈሩ መነሻነት ህዝብ መሬትን አፈር መዋትን ምዝማዝ ወዘተ በምስራቅ አፍሪካ ሁለት ጦርነት እንጀራቸው የሆኑ መሪዎች በአዲስ አበባና በአስመራ አሉ። እነሱ እስካሉ ድረስም የጥይት ድምጽ የፍንዳታ ጭሆት የአፍሪካ ቀንድን ጆሮ ያደነቁራል። ሰሞኑን ኢሳያስ አፈወርቄ ከኤርትራ የተናገሩትና
0:46 ባለፈው አንድ አመት ተኩል አብይ ከአዲስ አበባ ያደረጉት ነገር በርግጥም ቀጠናው ላይ አንዳች እልቂት በድጋሚ እያንዣበበ መሆኑን የሚጠቁም ነበር። ይህ የእልቂት ምድር ደግሞ የአፋር ክልል ክልል እንዲሆን የተፈረደበት ይመስላል አብይ አህመድ በትግራይ የተቋቋመ እና እኔ አቋቋምኩት ነው የሚሉትን መስተዳድር የሚወጋ ታጣቂ ሃይል እያደራጁበት ነው። ለዚህም ገዶ እና ተስፋ የተባሉ የጸጥታ እና መከላከያ ሰዎች ከትግራይ ተገፍተው እና ተከፍተው ከወጡ ጀነራሎች እና ታጣቂዎች ጋር ተጣምረዋል። የኦህደድ ብልጽግናዎች ኤርትራን የሚወጋውን የቀይ ባህር አፋሮችም የሚያስታጥቁት በዚሁ ክልል ነው። ኢሳያስ አፈወርቂ የአፋር ክልል ታጣቂዎችን እያስኮበለሉ ወደ ኤርትራ እያሻገሩ ናቸው። በተያያዘው ሳምንት ከአንድ ዞን የጸጥታ ሰራተኞች እና ፖሊሶች ነቅለው ወደ ኤርትራ
1:34 ምድር ገብተዋል። ሰሞኑን ባደረጉት ንግግርም የአፋር ምድር የጦር ሜዳ እንደሚሆን ጠቁመዋል። የጅቡቲው ፕሬዝዳንት አፋርን በማስመልከት ከአዲስ አበባ የተያዘውን ፕሮጀክት ክፉኛ አውግዘውታል። ይህንንም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ጽፈውታል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ባሳለፍነው መጋቢት ከአፋር ወደ ጅቡት ሄደው የጠበቃቸው የኡመር ግሌ ፊት ቀዝቃዛ ነበር። በርግጥም የእጅቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሳቸው የተናገሩትን ከሰሙ ቆይተዋል። ዑመር ግሌን እና አልበሽርን አባራቸዋለሁ። ከዚህ አካባቢ ሽማግሌዎች መጥፋት አለባቸው ማለታቸውን ገና ከአመታት በፊት ከፈረንሳይዎቹ ሰምተዋል። አፋርን አንድ አደርጋለሁ የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አጀንዳ መሰሪ መሆኑ የገባቸው የሚመስሉት ግሌ አትረብሹን ሲሉ በአማርኛ መናገራቸው
2:20 ታውቋል። በዚህ መሃል ደግሞ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ገብታለች ኡመር ጊሌ ከሬድዮ ፍራን ኢንተርናት ኢንተርናሽሊ ጋር ባደረጉት ውይይት ኤምሬትስ አካባቢያችንን እየበጠበጠች ነው ብለዋል። ከዚህ ንግግራቸው ውስጥ ቂም ሳይሆን እውነት አለ። አፋርን ጦር ሜዳ የሚያደርገውን ሁኔታ ለማግኘት ክሩን ስንከተል አቡዳቢ እናገኘዋለን። የጨዋታው አዘጋጅ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ስትሆን የጨዋታው ተሳታፊዎች አስመራ አዲስ አበባና ጅቡቲ ናቸው። ኳስ ሜዳው የአፋር ህዝብ ሲሆን ኳሷ አሰብ ነች። የውልደት ምጣኔው እጅግ ዝቅተኛ የሆነው በቁጥር የሚያነሰው በተበታተነ ሁኔታ በሶስት አገራት ውስጥ የሚኖረው የአፋር ህዝብ ምናልባትም እስከ መጨረሻው ሊጠፋ ወይም ድጋሚ ላንሰራራ የሚችልበት አደገኛ ጦርነት ተደቅኖበታል። ይህንን አፋርን የማጥፋት አቅም ያለውን
3:09 የእልቂት ዘመን በማስተባበር ደግሞ የአፋር ክልል ከፍተኛ ሹማምንት አብረው እየሰሩ ናቸው። የጦርነት እና የጦር ማእከሉ አፋር የትግራይ የኤርትራ የኦህዴድ ብልጽግና የጸረ ሻቢያ የጸረ ብልጽግናና መሰለ ሃይሎች ታጥቀው የመሸጉበትና የሚንቀሳቀሱበት እንደሆነ እንዲሆን ያደረገው ወቅታዊ ሁኔታ አደገኛውን አዝማሚያ መመልከት የዚህ ዝግጅት ትኩረት ይሆናል። በዝርዝር ለመመልከት ያስችልን ዘንድ የዲፕሎማቲክ እና የጸጥታ ምንጮችንና ባለሙያዎችን አነጋግረናል አብራችሁን ቆዩ። በሁሉም ክልሎች ግጭት አለ በሁሉም ክልሎች መጋደል አለ ትግራይ ክልል ግን የለም እነሱም አያፍሩም እኛ ብቻ ነን ሰላም ይላሉ ትንሽም አያፍሩም
3:55 አንዳንድ የውጪ ሰዎችም ሳይቀሩ ሰላም እኮ ያለው እዛ ብቻ ነው ይሉናል። አዎ ሰላም እዛ አለ ምክንያቱም ሰላም የሚያደፈርስ ሃይል ከዚህ ቀን ከሌት የሚሰራ ሃይል የለም። ደግሞም አያፍሩም እኛ ብቻ ነን ሰላም ይላሉ የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ስለራሳቸው ሃገር የተናገሩት ባይመስልም የሚያወሩት ስለ ትግራይ ክልል ነበር። በ2013 ዓ.ም ምህረት አሁን ኢትዮጵያን መቀመቅ ውስጥ የከተተውን እልቂትን ከማወጃቸው በፊት ደጋግሞ የሚናገሩትም ይህን ነበር። ያኔ ሃገሩን ሁሉ ሲያተረማምሱት የትግራይ ክልል የሰላም ደሴት ነበረች። በዚህ የተበሳጩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ እየተናገሩ ሌላው ሁሉ ተበጥብጦ እንዴት ትግራይ ሰላም ይሆናል ብለው ሚሊዮኖችን ሊገድሉ ዘመቱ። ያኔ የለኮሱት እሳት ተቀጣጥሎ ትግራይንም አቃጥሎ መላ ኢትዮጵያን እያነደደ ቆይቶ
4:43 አሁን ደግሞ ኤርትራ ላይ ሊለኮስ ጫፍ የደረሰ ይመስላል በ2013 ዓ. የወጉት የእኔ ገባር ሆኖ እንደ አገኘሁ ተሻገር የሚታዘዘኝም ስለኔ እንደ ሙስጠፋ ያለ ሎሌ እንደ አሸውጣ ሰው ያለ ሹምባሽ ከትግራይ አልገኝ አለ ብለው ነበር አሁን ደግሞ ጀነራል ታደስ ወረደ እኔ የሾምኩት ፕሬዝዳንት ነው ብለውም ራሴ አቋቋምኩት ያሉትን የክልሉን መንግስት የሚወጋ ታጣቂ ሃይል በአፋር ክልል እያደራጁ መሆናቸውን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግቧል። በህወሃት ተገፍተው እና ተከፍተው ከትግራይ እና ከሰራዊቱ የወጡ ሃይሎችን ለማደራጀት እና ለማስታጠቅ ደግሞ በሶማሊያ የጎሰ አለቆችን ሲያስታጥቁ የሰነበቱት ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ተመድበዋል። ባለፈው አመት በሶማሊያ ሲያደርጉት ከነበረው ተሞክሯቸው በመነሳትም ከትግራይ የተገፉ እና የተከፉ ሰዎችን በሽከት እና
5:29 መጋለያ በማደራጀት የቀደመውን የመከላከያ ልብስ በመስጠት የቡድንና የግለሰብ ትጥቅ በማቅረብ የራሳቸውን መንግስት ለመውጋት የሚያስችላቸውን ሃይል እየፈጠሩ ናቸው። አለላረ ኑ ይሄንን በአፋር ክልል የሚቋቋመንና የትግራይ ተወላጆች የተሰባሰቡበትን ሃይል በሚያደራጀው የብልጽግና አመራር ውስጥ የሚገኙት ደግሞ አቶ ገዱ ሃመሎ የተባሉት የክልሉ የጸጥታ ሹም ናቸው። በኦህደድ ብልጽግናዎች ዘንድ እንደ ታማኝ ተላላኪ የሚቆጠሩት እኚህ የጸጥታ ሹም ለዚህ አበርክቷቸው ከጨው ንግድ እስከ ሲሚንቶ ችርቻሮ ያለካይ እንዲያከናውኑ በመፍቀድ ውለታቸው እየተከፈላቸው ነው።
6:16 ይህ የትግራይ ተወላጆች የተጠራቀሙበት ስብስብ በአፋር ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀስና የሚደራጅ ታጣቂ ሃይል ነው። እነዚህን ብልጽግና ሀብት መድቦ ሰው አሰማርቶ የሚያደራጃቸውን ታጣቂዎች ደግሞ የቀድሞ የቲዲኤፍ አመራር አባል የሆኑት እነ ጀነራል ወዳንጥሩ ወይም ጀነራል ገብረ እግዚአብሔር በየነመሯቸው መሆናቸውን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ጽፏል። አለም እያየው የፈረመው የሰላም ስምምነትም የሀገሪቱ ህግም ሆነ የሞራል አልደንብ የማይገዛው የብልጽግናው መንግስት የራሱን ሀገር ሰዎች ለማገዳደል እንዲህ ተግቶ እየሰራ ነው። አብይ አህመድ እና ምስለኔዎቻቸው ጦርነት እንጀራቸው ነው ሲባል ለውጊያ የሚሆን አጋጣሚን ሁሉ ይጠቀማሉ ማለት ነው የምትል አንድ የቀድሞ የትግራይ ክልል መንግስት ባልደረባ የትግራይ ክልል ፖለቲካዊ ችግር በፖለቲካ መንገድ እንዲፈታ እንደ መሪ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣት
7:03 እየተገባቸው የራሳቸውን መንግስት ለመውጋት ሃይል ለማደራጀት ይሰማራሉ ትላለች። የታጣቂ ሃይል በአፋር ውስጥ ሲደራጅ ዝም ያለው የአፋር ህዝብ ግን መጥፊያው መሆኑን ሊገነዘብ ይገባል ትልና የክልሉ ባለስልጣናት የኦህደድ ብልጽግናን የጥፋት እና የእልቂት አጀንዳ እያስተባበሩት መሆኑ ሊገለጽለት ይገባል ትላለች። ፋይተር ሬድ ፋርክራቲክሽን ይሄኛው የአልጄራ ዘገባ ደግሞ አፋር ክልል የትግራይ ታጣቂዎች መደራጃ ብቻ ሳይሆን የኤርትራ ተቃዋሚዎችን ምሽግ መሆኑን የሚገልጽ ነው። የቀይ ባህር አፋሮች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት የሚባለው ታጣቂ ሃይል ኢሳያስ አፎርቅን ኢላማው አድርጎ የሚታገል ቡድን ነው። ይህንን ቡድን ለማጠናከር ደግሞ
7:49 የብልጽግናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሰውና መሳሪያ ማሰማራታቸው ከተነገረ ቆይቷል። አልጄራ ኢትዮጵያ ተደግፋቸዋለች ሲል የጠቀሰውን የዚህን ድርጅት አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንድ አመት በፊት ወደ አፋር ክልል በሄዱ ጊዜ ስለማነጋገራቸው ሲዘገብ ነበር። ይህም በኦህደድ ብልጽግና የሚደገፍና በአፋር ክልል የሚገኝ ሌላ ታጣቂ ታጣቂ ሃይል ነው። ይህንን ታጣቂ ሃይል ከባድ መሳሪያዎች ጭምር እንዳስታጠቁት እና በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ እየተንቀሳቀሰም እንደሆነ ተዘግቧል። የሃገሪቱን ሀብት በሀገር ውስጥ ለመገዳደያ መዋሉ ሳይበቃው የጎረቤት ሃገር ታጣቂንም ለማስታጠቅ የተጠቀመበት አገዛዙ አፋርን የደም መሬት ሊያደርገው የትግራይን ብቻ ሳይሆን የኤርትራን መንግስት የሚወጋ ሀይል ያደራጅበታል። ከቀይ ባህር አፋሮች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት በተጨማሪ ብርጌድን አህመዱ በዚሁ በአፋር ክልል ወታደራዊ ስልጠና
8:38 መጀመሩን በመግለጽ ደጋፊና አባሎቹ እንድንመዘገቡ ጥሪ ሲያቀርብ ተሰምቷል። ይህም በኦህደድ ብልጽግና የሚደገፍ በአፋር ክልል ውስጥ የሚገኝ ሌላኛው ተጨማሪ ታጣቂ ሃይል ያደርገዋል። የታጣቂዎች ማእከል የሆነው አፋር እንዲህ ያሉ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ታጣቂዎች መተረማመቻ ሆኗል። የራሱን ክልልም የጎረቤት ሃገርንም የሚወጋው እና ለመውጋት የውክልና ጦርነት የሚያካሂደው የሆደድ ብልጽግና ይህንን እንደ ችሎታና ብልጠት ሲያየው እንደ መመልከት ያለ አስተዛዛቤ ነገር የለም የሚሉ አንድ የአፍ አፋር ፖለቲከኛ መንግስታዊ ስልጣን ያስገኘውን ሃብት እና ሃላፊነት የራስንም አገር ለማተረማመስ ጎረቤትንም ለማመስ መጠቀም አላዋቂነትና አገር ጠልነት ነው ይላሉ። የኦህደድ ብልጽግና ቀይ ባህር ላይ ኢሬቻን አከብራለው ብሎ መናገር ከጀመረ ወዲህ
9:23 ከአስመራው የቅድመ ወንጀል አጋሩ ጋር በይፋ መለያየቱ ታውቋል እናም የአፋር ህዝብ በጦርነት ይጠፋል በቁጥርም እየተመናመነ ያለ ህዝብ ነው ከኤርትራ ጋር በሚደረግ ውጊያ ስለሚጠፋ የከሚሴ እና የአካባቢውን ኦሮሞ ወደ አፋር እናካልለዋለን ከኦሮሞ ኦሮሚያ ጋር በጉርብትና የቆየው አፋርም በእኛ ይጨፈለቅና ክልሉ የኦሮሞ ይሆናል። ኦሮሞም ከቀይ ባህር ጋር በቀጥታ ይገናኛል ብለን የኦሮሞን ህዝብ እንቀቅሰዋለን እናሳምነዋለንም የሚል አውዳሚ ስሌት እንዳላችሁ አውቃለሁ የሚሉ አንድ የቀድሞ የብልጽግና ሹም ደግሞ ይህንን በማስተባበር ሂደት ውስጥ የአፋር ልሂቃን እየተሳተፉ መሆኑ አስተዛቢ ነው ይላሉ። ህዝብን መሬትን አፈር ከመድረክ መጣዎትን ምዝማዝ ወዘተን
10:16 የኤርትራው ፕሬዝዳንት እንኳን እንዲህ ያለ ለማፈር አግኝተው እሳቸው የጦርነት ችግኝ መትከል የሸበቱበትም የመለጡበትም ሁለት ጸጉር ያወጡበትም ስራቸው ነው። የአፋር ክልልን እንዲህ በስም ጠቅሰው የአፋር ህዝብና መሬቱን ለሚያመቻቸው ሴራ መጠቀሚያ ማድረግ የብሄር ጦርነትን በሁሉም ቦታዎች ማቀጣጠል ወዘተ እያሉ ዘርዝረዋል። የዚህ ንግግራቸው ምንጭ በፍቅራቸው ዘመን ከኦህዴ ከደድ ብልጽግናዎች ጋር የመከሩበትና ያወቁት ጉዳይ ስላለ ብቻ አይመስልም። የአፋርን ህዝብ ምድር አኬልዳማ የማድረጉን እቅድ እሳቸው ሰተት ብለው ገብተውበታል። የብልጽግናው አገዛዝ የኤርትራን እና የትግራይን ታጣቂዎች ካስጠለለበት የአፋር ክልል ወደ ኤርትራ የሚኮበልሉ የጸጥታ እና የደህንነት ሰዎችን እየተቀበሉ እያስታጠቁ እና እያደራጁ ናቸው። በዚህ በተያዘው ሳምንት ከአፋር ክልል ዞን ሁለት ቁጥራቸው ያልታወቀ የመንግስት
11:01 ወታደሮች ወደ ኤርትራ መሄዳቸው ተሰምጧል። ከብርሃለ ወደ ኤርትራ የተሻገሩት እነዚህ ታጣቂ ሃይሎች ከሃጂ ከሃጂ ኢብራሂም ሃይሎች ጋር መቀላቀላቸው ተዘግቧል። ሃጂ ኢብራሂም ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሃመድ አጎት ሲሆኑ ከአፋር ክልል ውስጥ አጃቢዎቻቸውን ይዘው ወደ ኤርትራ የኮበለሉና በዚያም ከሄዱ በኋላ ታጣቂ ሃይል እያደራጁ ያሉ መሆናቸውን የገለጹ ናቸው። እሳቸው በሰጡት አስተያየት ዋና አጀንዳቸው የአወል አርባን አገዛዝ መዋጋት እንደሆነ ገልጸው የሙስጠፋ መስተዳድርም የአፋር ህዝብ ጠላት ነው ብለዋል። እዚህ ጋር የሚነሳው ጥያቄ ከኦህደድ ብልጽግና ጋር ጸብ ውስጥ የገባው የሻቢያ አገዛዝ የአፋር ክልል መንግስትን ብቻ ኢላማ ያደረገውን የኢብራሂምን ታጣቂ ሃይል መደገፉ ምን ትርጉም ይሰጣል የሚል ሊሆን ይችላል። አስተያየት ሰጪዎች ለዚህ የሚሰጡት ምላሽ የኢሳያስ እና ሻቢያውያን ፍላጎት
11:48 ኢትዮጵያን የትኛውንም ክፍል ላይ ቢሆን መበጥበጥ እንጂ አብይን ማስወገድ አይደለም ይላሉ። የሻቢያ የእድሜ ዘመን ፍላጎት ኢትዮጵያን ማመስና ማፍረስ ነው። ይህንን በተግባር እየፈጸመ ያለው የኦህደድ ብልጽግና ደግሞ እንዲወገድ ሻቢ አይፈልግም። ይሁን እንጂ በሃገር ውስጥ እርስ በርስ መተላለቁ እንዲቀጥል የትኛውንም ሃይል እያስታጠቀ እና እያሰለጠነ ሊያሰማራ ይችላል የአፋር ታጣቂዎችን የሚደግፈውም ከዚሁ አንጻር ነው ሲሉም ያብራሩታል ሻቢያዎች በአሰቡ ወደብ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኘው የአፋር ክልል ላይ የሚለኮስ እሳት ግዛታቸውን ከእህደድ ብልጽግና ወረራ ለመከላከል የሚደረገው ጥረት አካል አድርገው ሊጠቀሙበት ይችላሉ ሲሉም ያክላሉ ለዚህም ይመስላል ባለፉት አመታት የብልጽግናን መንግስት አግዘው ኢትዮጵያውያን የጨፈጨፉት እና በዚህ ስራቸውም እንደማይጸጸቱ የተናገሩት ኢሳያስ አፍ ወርቂ
12:37 የኢትዮጵያ ህዝቦች ሊታገሉ ተነስተዋል የሚል አስተያየት ሲሰጡ የተሰሙት ተቃውሞቱ ከባተል ይህ የኢሳያሳ ፎርቂ ገለጻ ኢትዮጵያን እዛው እየተላለቃቹ ትቀጥላላችሁ የሚል ትርጉም ቢሰጠው ልክ ይሆናል የኢትዮጵያ ህዝቦች የራሳቸውን ምርጫ ወስደዋል ተቃውሟቸውም ለማጠናከር እየተዘጋጁ ነው የሚለው ገለጻ እስካሁን በብልጽግና ላይ የተካሄደው ተቃውሞ እና ጸረ አገዛዝ ትግል የሚረባ አልነበረም አሁን ግን እኛ ልንደግፈው ስለሆነ ይጠናከራል በአገዛዙ ላይ የሚደረገው ተቃውሞም ገና ዝግጅት ላይ ነው እንጂ አልተጀመረም የሚል መሆኑም ግልጽ ነው የብልጽግናን አገዛዝ የኦሮሞ ወጣቶች
13:24 ገና ከ11 አጋማሽ ጀምሮ የትግራይ ህዝብም ገና ከማለደው አንስቶ የአማራ ወጣት ባለፈው ሁለት አመት እየታገሉት ቢቆዩም ይህ ሁሉ በኢሳያስና በሻቢያውያን ፈቃድ የተካሄደ ስላልሆነ እንደ ትግል አይቆጠርም እናም በአደባባይ የኢትዮጵያ ህዝቦች የራሳቸውን ምርጫ ወስደዋል ተቃውሟቸውን ለማጠናከር እየተዘጋጁ ነው በማለት ፀረ አገዛዝ ትግሉ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው እኛ ስንቀባው ነው ስንመርቀውም ነው የሚል መልክት በአንድ በኩል እስከ ዛሬ የነበረው ትግል ሁሉ የረባ አልነበረም ትግሉ ገና አሁን መጀመሩ ነው የሚል ሃሳብ ደግሞ በሌላ ወገን አስተላልፈዋል ይህ ብልጽግና የሚወደው መንገድ ነው እናም ከሻቢያ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሚደረግ ውጊያ አፋር አኬዳማ ይሆናል ማለት ነው። ብልጽግና የሚደግፋቸው ጸረ ሻቢያ ታጣቂዎች በአንድ በኩል ሻቢያ
14:09 የሚያስታጥቃቸው ጸረ ብልጽግና ኃይሎች በሌላ ወገን ከሚያደርጉት ውጊያ በተጨማሪ ራሳቸው መንግስታቱ አሰብን ለመያዝ እና ለመከላከል በሚያደርጉት ጦርነት የአፋር ህዝብ ወደ ታሪክነት የሚቀየርበትን መቃብር ይከፍቱታል። ከነዚህ የጦርነት አባራዎች በተጨማሪ የጂቡቲው ፕሬዝዳንትም በዚሁ ሂደት ውስጥ ሚና እንዳላቸው እየተነገረ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባሳለፍነው መጋቢት አደም ፋርሃን እና አህመድ ሺን ይዘው ጅቡቲ በሄዱበት ወቅት ወቅት አፋርን አንድ ማድረግ እቅድ አለኝ ብለው በመናገራቸው ኡመርጊሌ ተቆጡ የሚሉ ምንጮች ከዛ በኋላም የጅቡቲ መንግስት በሃገሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ማሳደድ ገባ ይላሉ። አፋርን አንድ አደርጋለሁ ማለት በጅቡቲ እና በኤርትራ የሚኖሩትን አፋሮች ወደ ኢትዮጵያ እጠቀልላለሁ ማለት ነው የሚሉት ቀደም ሲል የጠቀስናቸው የአፋር ጉዳዮች ታዛቢ ይህ ደግሞ
14:55 የጅቡቲሉ ሉዓላዊነት የሚጻረርና ግዛታዊ አንድነቷን አደጋ ውስጥ የሚጥል ነው ይላሉ እናም ይህንን አፋርን አንድ የማደርግ ሃሳብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሙ በኋላ በቁጥር አናሳ መሆናችን እንድንዋጥ ያደርገናል በሚል ኢትዮጵያንን ከጅቡቲ ማባረር ተጀምሯል። ይህንን የአፋሮችን አንድ ማድረግ እንቅስቃሴ የሚያኮላሹ ተግባራትንም ወደ መከወን ተገብቷል ሲሉ ያክላሉ። ከዚህ ኢትዮጵያን ከማባረር በዘለለ በጅቡቲ መንግስት የሚደገፉ ጸረ አፋር ሃይሎችም እንዳሉ የሚያነሱ ሰዎች ደግሞ እነዚህም ትጥቅ ይሰጣቸዋል ይላሉ። ከወራት በፊት የጅቡቲ መንግስት በድሮን የደበደባቸው የዑመር ግሌን አገዛዝ የሚዋጉ ታጣቂ ሃይሎችም በዚሁ በአፋር ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ሲዘገብ መክረሙ አይዘነጋም። በአጠቃላይ አፋር ክልል በብልጽግና የሚደገፉ ሁለት ጸረ ሻቢያ
15:41 እና አንድ ጸረ ህወሃት ታጣቂዎች በሻቢያ ስንቅም ትጥቅም የሚሰፈርለት ቢያንስ አንድ አማይል በጅቡቲ የሚደገፉ የተበታተኑ ታጣቂዎች የጅቡቲን መንግስት የሚቃወሙ ሃይሎች የሶማሌ ክልሉ ሙስጠፋ መሃመድ የሚጠቀሙባቸው ታጣቂዎች በአጠቃላይ በሶስት ሃገራት የሚደገፍና ሶስት ሃገራትንም የሚቃወም ቢያንስ ሰባት ታጣቂ ሃይል ነፍጥ ይዞ ይዞ የሚንቀሳቀስበት ክልል ሆኗል። የስልጣን ዘመኑን መክሊት ጦርነትን ያደረገው የብልጽግናው መንግስት የአፋርን ህዝብ እስከ ወዲያኛው ሊያጠፋው የሚችልበትን ይህንን ታጣቂ ሃይልም እያተረማመሰው ነው። መልካሙን ሁሉ በመመኘት በዚሁ እንሰናበታለን [ሙዚቃ]