0:04 [ሙዚቃ] ይህ መተቀፍ አሁን ወደ መነቃቀፍ ብቻ አልተቀየረም። ይህ ፈገግታ አሁን በተቆጡ ገጾች ተተክቶ አልበቃውም። ይህ መገናኘት አሁን አይንህን ላፈራባ ብሎ አላቆመም። ወደ መጠቃት እና መታኮስ ተለውጧል። ሁለቱ መሀመዶች መሀመድ ቢንዛይድ እና መሃመድ ቢንሳልን እንደ ታናሽ እና ታላቅ የሚታዩ አንዱ መምህር ሌላው ደቀ መዝሙር ሆነው ይኖሩ ነበሩ። ሁለቱ ዞኖች ፍቅራቸው ከሳውዲ በራህ የሞቀ ከኤምሬት ስም ከተሞች የደመቀ ነው ተብሎ ተወርቶለትም ነበር። አሁን ያመዋደዳቸው ነበር ሆኖ ቁጣቸው እንደ
0:51 አራስ ነብር ሆኗል። ወዳጅ አይጥላህ የሚለው ተረት ወዳጅ አይጣላህ ቢባልም ልክ ነው። እስከ ጥግ የተዋደዱ ይመስሉ የነበሩት ሁለቱ ሰዎች እስከ ጫፍ እየተጣሉ ናቸው። አንዱ በአንዱ ይዞታ ላይ ቃታ መሳብ ጀምሯል። የባህረ ሰላጤው ባህር በፖለቲካ ሳይሆን በደምና ብረት ቀልቷል። ሰሞነኛው የመካከለኛው ምስራቅ ቁጥረት በኤምሬት እና በሳውዲ መሪነት የደም ግፊቱ ጨምሯል። ሁለቱ መሀመድ ቢኖች ተፋቅረው የገቡበትን ዘመቻ ተናበው ያካሄዱትን ድርጊያ የልዩነታቸው ምንጭና የአቅማቸው መፋተሻ አድርገውታል። የሳውዲ እና የኤምሬት ፔትሮ ዶላር የጡንቻው አው ፈርጣማነት የዲፕሎማሲው ጉልበትና ወታደራዊ የበላይነት ይለካበት ዘንድ አውደ ውጊያ ተከፍቷል። ይህ አውደ ውጊያ ሻርጃ ወይም ጅዳ
1:37 አይደለም ዲያቢ ወይም ርያድም አልሆነም በዱባይ አልያም በመዲናም አልተከሰተም እነዚህ የአረብ ተቀናቃኞች በነሱም ሀገር ሆነ በነሱ ዜጋ አይዋጉም የሚተኩሱት በቀጠሯቸው ሰዎች የሚታኮሱት ደግሞ በወረሯቸው አገሮች ነው። በዚህ ዙር የመፋለሚያ ምድር ያደረጓት ሁለቱ ዞኖች ለሳር የመረጧት ሜዳ የመን ነች። ሁለቱም ጉልበተኞች ወደ የመን የገቡት ተጠራርተው የጋራ እቅድ አውጥተው ወዳጆቻቸውን አሰልፈው ቅጥር ተዋጊዎቻቸውን ገዝተው ነበር። ከ10 አመት በፊት እነዚህ ሁለት ሰዎች እነዚህ ሁለት መሪዎች የመን የገቡት ፍቅራችን እስከመቃብር ነው ብለውም ነበር። ዛሬ ግን አንዱ ለሌላው መቃብርን እየተመኘ ነው። ለዚያውም በየመን ጉዳይ ለዚያውም በየመን ምድር የተባበሩት አረብ
2:23 ዕምሬቶችና ሳውዲ አረቢያ በየመን ምክንያት ተጣሉ ወይስ የመን የጸባቸው መገለጫ መግለጫና መግለጫ ሆነች ከጸጉ ጀርባ ያለው ጉዳይ ከክብር ከሀብት ቅርምት ከቀጠናዊ ፉክክር እና ከመሰል ነገሮች የዘለለ ይሆናል ወይ ሁለቱ መሃመዶች ከመጋረጃው ጀርባ የተቋሰሉበት ነገር ምንድነው ለመሆኑ ያ ፒምር የሚያጓርስ ፍቅራቸው ያንድ ድንኳን ከአሸዋ ላይ የሚያዝናናቸው መዋደድ በምን ምክንያት ወደ ጸብ ገባ በየመን የተጀመረው የፀብ ክርስ የት ይበጠ ሲሆን ራሳቸውን ችለው የማይጣሉት ጀሌ ካላስከተሉ የማይዘምቱት እንደ አብይ አህመድ እና ኢሳይያ እያሳፍ ወርቄ ያሉ ተላላኪዎችን መቅጠር የሚወዱት ሁለቱ መሃመዶች ጸባቸው እንደ ኢትዮጵያ ላሉ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ይተርፊውን ወይ? እነዚህ ሁለት መሪዎች የተዋጣላቸው ጓደኛሞች ብቻ ሳይሆኑ የሚያከብሯቸውም
3:10 የጋራ ወዳጆች የነበሯቸው ናቸው። ታዲያ ስለምን እነዚህ የጋራ ወዳጆች ሸምጋይ ሆነው አልመጡም። ደግሞስ ከመካከለኛው ምስራቅ እነዚህ ሁለት ሀገሮች የሚነጋገዱትን ያህል ሌላ የለም እና ይጨካከናሉ ወይ? እነዚህን ጥያቄዎች ግራና ቀኝ ለመመልከት የሚያስችሉንን ሰነዶች አገላብጠናል አብራችሁን ቆዩ። [ሙዚቃ] እነዚህ ሰዎች አብይ አህመድ እና ኢሳያ ሳፍ ወርቂን ለማፈራረም ብዕር እና ወረቀት ብቻ ሳይሆን ደረትን አልፎ የሚዘረጋ የአንገት ወርቅም አቅርበዋል። ብልጽግና ሲነግስ ረብጣ ዶላር ይዘው ማልደው አዲስ አበባ ተገኝተዋል። የአልቦራንን እና ሄቲን መፈንቅለ መንግስት ለመደገፍ ካርቱም ሄደው የሚደጋገፉ ነበሩ። በግብጽ
3:57 ኤልሲሲ ሙስሊም ብራዘር ሱድን አባረው ወደ ስልጣን ሲመጡ አጋፋሪዎቹ አቡ ዲያቢ እና ሬያድ ነበሩ። መላረብን በካታር ላይ ሲያሳምጹ በጋራ ነበር። መሀመዶች ሶሪያንም ሆነ የመንን፣ ጋዛንም ሆነ ሊቢያን፣ ኢራንንም ሆነ ፍልስጤምን የሚመለከቱበት መነጽር አንድ አይነት ነበር። እነዚህ ሁሉ ነበሮች አሁን በመታኮስ ተተክተዋል። በርግጥም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ሳውዲ አረቢያ በአንድ ወቅት የአንድ ሳንቲም ሁለት ጀርባዎች ይመስሉ ነበር።ለአንድ አላማ የተሰማሩ ለአንድ ግብ የተፈጠሩ ይመስሉ ነበር እንደውያን አቆጣጠር በ2015 መጋቢት ወር ላይ መላ አረብ ክተት ብለው ወደ የመን ሲዘምቱ ዛሬ እንዲህ ያለው ውጤት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ የጠበቀም አልነበረም የነገሩ ስራ መሰረት የአለምባቱ ሰሞን የሚጀምረው በሳውዲ መሪነት ወደ የመንገብተው
4:44 ውጊያ ከጀመሩ ከአምስት አመታት በኋላ እንደ ኤሮፒያን አቆጣጠር በ2019 ነበር። በ2015 ዘመቻው ሳውዲ መሪ ይሁን ተብሎ ከ10 በላይ አገራትም ተሳትፎበት በየመን ዋና ከተማውን ኦንሰና የተቆጣጠሩትን እና በኢራን የሚደገፉትን የሃውቲ ታጣቂዎች ለመውጋት ቀድማ የተገኘችው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ነበረች። በቀጥታ እየተሳተፈች ከላቲን አገራት ከኤርትራ እና ከሱዳን ቅጥር ተዋጊዎችን እየገዛች ጭምር እየተዋጋች በአሰቦ ወደ ላይ የድሮን ቤዝ እየከፈተች ከሳውዲ ጋር በጋራ እቅድ በጋራ ስትዋጋ ከርማለች የተባበሩት አረቢ ኤምሬቶች ጦርነቱን በድል ማጠናቀቅ ሳይችሉ ሃውቲዎችና ለቃቸው ኢራን ሳይሸነፉ ይልቁንም የመንን ለሁለት ሰንጥ ጥቃት እያለ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በድንገት ጥላ
5:29 መውጣቷን አወጀች ኦፕሬሽኑን አቋርጣ ወጣዋለች አሰብ ላይ የተከራየችውን የጦር ሰፈርም ዘጋችሁ ለመውጣቷ ምክንያት ያደረገችው ጦርነት አላዋጣም ሰላም ይሞከር ብላ እስትራቴጂካዊ ለውጥ ነው ብላ ነበር ይሁን እንጂ አወጣ ጦርነቱን በውክልና እና በቅር ለመቀጠል በአካል ያላትን ተሳትፎ ለመተው ወይም ለመቀነስ ነበር መሃመድ ቢንዛይድ መሃመድ ቢንሳልን ጥለዋቸው ሲወጡ በጦርነት የፈረሰችው የመንሳውዲ እና ኤምሬት ባስተባበሩት ዘመቻ ተሰነጣጥ ነበር። ደዋ እና ሰሜናዊ የመን ተብላ ሃው ሰሜናዊን ፍንካች ዋና ከተማቸውን ሰና አድርገው ጸመድ ቢንዘይድ እና መሃመድ ቢንሳልን ደግሞ ደዋዩን ክፍል መናገሻውን ኤደን እንደሆነ አድርገውት ነበር። ደዋይ ክፍልም እንደገና የተለያየ አቋም
6:15 ባላቸው የፖለቲካ እና የትጥቅ ሃይሎች ለሁለት ተከፈለኛው ወገን ሳውዘር ትራንዚሽናል ካውንስል የሚባል ሲሆን ደቡን ክፍል ክፍል የመገንጠል ግብ ያላቸው ሃይሎች የተሰባሰቡበት ነው። ይህ ተገንጣይ ሀይል ደቡባዊ የመን ያ ከሺ 1967 እስከ 1990 የነበረው አገር ያ ከነ መንግስቱ ያለማርያም ጋር አብሮ ይሰራ የነበረው ብቸኛው ሶሻሊስታዊ አረብ አገር እንዲፈጠር የሚሰራ ነው። እኛ ሰነአ ላይ ጉዳይ የለንም እኛ እራሳችንን ችለን አገር መሆን አለብንም ባይ ነው። በዚህ ደዋይ ክፍል ላይ ያለው ሁለተኛው ፍንካሽ ደግሞ የመን ሰሜንም ሆነ ደብ ተብሎ ነገር የለውም አንድ ሃገር ሃገር ነው። በሰናሉ የሃውቲ ታጣቂዎች ተሸንፈው መንግስታችን ወደ ዋና ከተማው መመለስ አለበት ሀገራችንም አንድ ነች የሚል የአንድነት ሃይል ነው። በአለም
7:03 አቀፉ ማህበረሰብም እንደ መንግስት የሚታይ ስብስብ ሲሆን ፕሬዝዳንሻል ሊደርሺፕ ካውንስል የፕሬዝዳንታዊ አመራር ምክር ቤት የሚል መጠሪያ አለው። የሁለቱ መሃመዶች አስተላለፍ ወደ ሰሞነኛው ደም መፋሰስ የሚቀየረው እዚህ ጋር ሲደርስ ነው። ሳውዲ አረቢያ የአንድነት ሃይሎችን ደግፋ ስትቆም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ደግሞ ተገንጣዮቹን እንዲሳካላቸው ትጥቅም ስንቅም መስፈር ቀጠለች። ደቡባዊ የመን የሁለቱ ጉልበተኞች የውክልና መፋለሚያ ሆኖ በቀጠለባቸው ባለፉት አመታት በኤምሬትስ የሚደገፉት ተገንጣዮች ሰሞኑን ከፍ ያለ ድል አስመዘገቡ። ከደቡብ የመን አብዛኛውን ክልል የነዳጅ ጣቢያዎችን፣ ከተሞችን፣ የኢብስና የባህር ቀጠናዎችን መቆጣጠራቸው ተዘገበ። ደጋፊዎቻቸው በየአከባቢው ወጥተው በልታና በደስታ ሲቀበሏቸው ታዩ።
7:50 >> አግባብ አይሰለንደውላ >> በእምሬትስ የሚደገፉት የደቡብ የመን ተገንጣዮች አለም አቀፍ እውቅና ያለውን እና በሳውዲ አረቢያ የሚደገፈውን የፕሬዝዳንታዊ አመራር ምክር ቤት እያሸነፉ አብዛኛውን ቀጠና ሲቆጣጠሩ ሬያድ በእልህና ቁጣ ተከሰተች የሳውዲ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ በየመን ያለው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንቅስቃሴ ሁሉ የሀገሩን ብሄራዊ ደህንነት እንደሚያሰጋ ጠቅሶ ለዚህ ስጋት እርምጃ እወስዳለው አለ። አክሎም በየመን ውስጥ ያሉ የተባበሩት አረመሬት ሃይሎች በሙሉ ለቀው ይውጡ ሲል ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ። እንዲህ አለ ከረር ያለ መግለጫ ከማውጣቱ ከሰዓታትም በፊት በሚደግፈው እና በኤደን ከተማ በሚገኘው የአንድነት
8:37 መንግስቱ ማለትም ፕሬዝዳንሻል ሊደርሺፕ ካውንስል በተባለው ምክር ቤት በኩል ኤምሬትስ በ24 ሰዓት ውስጥ የመንን ለቃ ትውጣ የሚል ቀጠሮ ሰአት ወይም አልቲማተም ሰጥቶ ነበር እዚህ ጋር አንድ ነጥብ ልብ ብለን እንለፍ የመን ለሳውዲ አረቢያ ጎረቤት ነች። በየመን የተነሳ ጦርነትም በቀጥታ ተጠቂ ሲያደርጋት ቆይቷል። እናም ነገሩ የብሄራዊ ደህንነትን የሚያሰጋ ነው ስትል ከዚህ ከጉርብተና ጂኦግራፊ ተነስታ ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ግን ከመን ጋር የምትጋራው አንድ ጋት ድንበር የለም። የመሀመድ ቢንዛይድ አገዛዝ ከየመን ጉዳይ እንዲወጣና እጁን እንዲሰበስብ ካልሆነ ግን እርምጃ እንደሚወሰድበት የገለጸው የመሀመድ ቢንሳልን መንግስት ከኤደንም ከሪያድም ያወጣው መግለጫ አድማጫ ይልቁንም ተገውዲ ወደዚህ ግዛቶች መጠጋት ቀይ መስመሬ
9:25 ነው ወደ አለቻቸው አካባቢዎች ገብተው ተቆጣጠሩ ሃድራማውና ማህራ የተባሉት ለሳውዲ የቀረቡት ቦታዎችም በነዚ ተገንጣዮች ቁጥጥር ስር አሉ ከሪያዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሆነ ከኤደኑ መስተዳድር የወጣውን የውጡልንና አትተንኩሱን ጥያቄ በዝምታ ማለፍ ያልወደደችው ያላትንም አቅም የተገነዘበችው ኤምሬትስ በየመን የነበረው የጸረ ሽብር ሰራዊቴ እንዲወጣ እያደረግኩት ነው ይህንን የማደርገው ግን ሳውዲ ስረዛች እና ስላዘዘችኝ ሳይሆን በራሴ ፈቃድ እና ለወታደሮች የደህንነት ስል ነው በማለት እነ ሳውዲ ባስቀመጡት የ24 ሰአት ጊዜ ገደብ ውስጥ እየለቀቀች መሆኑን ገለጠች እንዳም ሆኖ ነገሩ አልሸሹም ዞር አሉ አይነት ነገር ነበር ግጭት ባለበት አገር አገር አፍራሽ እና ገንጣይ ባለበት ሁሉ የማትጠፋው የተባበሩት አረብ እምሬት እየወጣው ነው እያለችም
10:11 ከሳውዲ አረቢያ አፍንጫ እየተዋጉ ግዛት የሚቆጣጠሩትን ተገንጣዮች መደገፏን ገፋችበት የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያንንቀቅ ጥቅምቻ ያለውን መግለጫ ካወጣ በኋላ የአቡዳቢው መስተዳድር እንደለመደው ተኳሽና ተተኳሽ በመርከብ ጭኖ ወደ ተገንጣዮቹ ይዞታ ላከ። የተላከው ከባድ የጦር መሳሪያም በነዳጅ ወደ በለጸገችው ሙካላ ከተማ ደረሰ። ሆኖም ከተገንጣቹ እጅ ሳይገባ በሳውዲ የጦር ጀቶች ተደብድቦ ዶጋ መድ ሆነ። ይህ ሆነው በፈረንጆቹ አዲስ አመቱ ዋዜማ ባሳለፍነው ማክሰኞ ነበር። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ንብረትነቱም ሆነ መነሻው የሷ የሆነው መርከብ እንዲህ ውዳመድነት ሲቀየር ቁጣና ብስጭት አላሰማችም ይልቁንም መርከቡም የኔ አይደለም ተገንጣዮችንም የማግዝ
10:58 አይደለሁም ብላ ሽምጥ አድርጋ አክዳለች የሳውዲ ስርወንግስት መገናኛ ብዙሃን ግን መንግስታችን የተመረጠ ደግሞም የተሳካለት ሲቪልና መሰረተ ልማት ያላወደመ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አካሂደናል እያሉ ናቸው። ሁለቱ ሀገራት እዚህ ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው በፊት ዲፕሎማሲ ሙከራ አድርጎ እንደነበር የሚያትተው የፋይናንሻል ታይምስ ዘጋቢው አንድሪው ኢንግላንድ ትንታኔ ይህም ሳውዲ ያደረገችው ጥረት ነበር የእምሬት ተደጋፊዎች በየመን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲቆም አቡዳቢ ይነገራት ዘንድ ለሳምንታት ምልጃል ነበር አልሆነም ነገሩ ወደ መታኮስ አደገ ብሏል። የሁለቱ መሃመዶች ጸብ ስራ መሰረቱ ግን የመን አይደለም የሚሉ ሰዎች መናናቅ የበላይነት ለመያዝ የሚደረግ ትግል እና ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ዋና ዋናዎቹ ሰበቦች ናቸው ይላሉ። አስተያየታቸውን
11:44 ለሮይተርስ ያጋሩ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን የሁለቱን መሪዎች ልዩነት የሚገልጹት በቀጠናው ቁልፍ ሰው ሆኖ ለመውጣት የሚደረግ ፉክር ያመጣው ግለሰባዊ ብልጫ ነው ብለው ነው። ወል እስቴት ጆርናል የሳውዲ አረቢያው ንጉስ መሀመድ ቢንሳልን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢንዛይድ እልም ባለጸብ ውስጥ ቅልጥ ባለኩርፊያ ውስጥ መሆናቸውን በጥልቀት ያጋለጠ ሚዲያ ነው። የሳውዲው ሰው የእምሬቱን ታላቃቸውን አለቀውም ማለታቸውን ጋዜጣው ጽፏል። ካታር ላይ ከወሰድሁትም የከፋ እርምጃ ይጠብቃል ማለታቸውንም እንዲሁ የሁለቱን ጸብ ዘቤ ኦፍ ፍሬኔስ በሚል ርእስ ነበር የጻፈው ወዳጅ እየመሰሉ የተጣሉ አብረው እየታዩ የተለያዩ እንደማለት ከሶስት አመታት በፊት በነበረው ታህሳስ ወር በአንዱ ቀን የሳውዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢንሰልን የሀገራቸውን ጋዜጠኞች በሬያድ ጠሩ ሁሉንም ጋዜጠኞች መቅረጸ ድምጻቸውን እና
12:33 የቴሌቭዥን ካሜራዎቻቸውን እንዲያጠፉ ካዘዙ በኋላ የማይጠበቅ መልእክት መናገር ጀመሩ ለአስርታት እንደ ወዳጅ ያቀረብናት አጋራችን መስሎ ያስጠጋናት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከጀርባ ወግታናለች ምን ማለት ማድረግ እንደምንችል አላወቁም አሳያችኋለው ሲሉ ተደመጡ >> ዋስት [ሙዚቃ] አላይሳውዲያ ዩኤልድል [ሙዚቃ] ፖለቲክ ጎልሽን ኮንፍሊክቲንግ ዋት ብሬክን [ሙዚቃ] >> ሁለቱን መሃመዶች ያቃቃራቸው ፖለቲካ እና የራስ ክብር ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ፉክክርም ነው የሚሉ ሰዎች ማስረጃ አላቸው ሳውዲ በነዳጅ ላይ ያለኝ የኢኮኖሚ ጥገኝነት ማብቃት አለበት እያለች ነው እናም በዱባይ የነበሩ ትላልቅ የምዕራቡ አለም
13:19 ኩባንያዎች ዋና ቢሮአቸውን ወደ ሬያድ እንዲያሻግሩ ከማባበል ወደ ማስገደድ ገብታለች ዋና ቢሮአቸውን ዱባይ ወይም አቡዳቢ አልያም ሌላ ኤምሬትስ ምድር ያደረጉና በሳውዲ ምድር ስራ ያላቸው የትኛውም ኩባንያ ዋና ጽህፈት ቤታችሁን እዚህ ካላደረጋችሁ ዘግታቹ ውጡ ተባሉ አልጋ ወራሽ መሃመድ ከፕሬዝዳንት መሀመድ አገር ከሚያስኮበልቸው ባለፀጋዎች ባሻገር በሃገራቸው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ማዕከል ለመገንባትም ያልማሉ በዚህም በርካታ ቱሪስቶችን በመሳብ ለዘመናት ኤምሬቶች የተቆጣጠረችውን የአረቡ አለም ንግድ መብለጥ ይሻሉ። በዚያው ሰሞን ይፋ ያደረጉት የናሽናል ኤርላይን ስም የኤምሬት ስን አየር መንገድ እንዲፎካከር ተልእኩ የተሰጠው ነው። ወዲህ ደግሞ በእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ውስጥ ሀብት ለማፍሰስ ስምሪት ላይ ናቸው። ሳውዲዎች ኒው ካስት ዩናይትድን ኤምሬቶች ማንቺስተር ሲቲን ገዝተው የእግር ኳስ አለም
14:07 ኮከቦች ደምቀው በሚታዩበት መድረክ ለመንጸባረቅ እየጣሩ ናቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን የእምሬቶቹ ፕሬዝዳንት በሳውዲው ንጉስ ላይ ጥርስ ርስ ነክሰዋል። በድብቅም የከፉ ጥፋቶችን ፈጽሟል ሲሉ አልጋ ወራሹን ይከሷቸዋል። የሁለቱ መሃመዶች ፀቱ ብዙ ነው የሚሉት አራቱ የወልት ጆርናል ዘጋቢዎች በየመን ጉዳይ እና በነዳጅ ላኪ ሀገራት ድርጅት ውስጥ ባሳዩት አቋምም አለመግባባት ውስጥ ሲገቡ ነው መሀመድ ቢንሰልን ያንን ዝግ ስብሰባ ከጋዜጠኞች ጋር ያደረጉት ይላሉ። አልጋ ወራሹ እንዲህ አሉ ለእምሬቶች የምንፈልገውን ዘርዝረን ልከናል ይህንን ሊቀበሉት አልወደዱም። የማይቀበሉት ከሆነ የከፋ እርምጃ እንደምወስድ ማወቅ አለባቸው። ምናልባትም በ2017 በካታር ላይ ከወሰድሁትም የባሰ ብለዋል። በርግጥ አልጋ ወራሹ ከዛን ጊዜ ወዲህ ተከታታይ ዲፕሎማሲያዊ
14:54 ስራዎች ውስጥ ተሰማርተው ታይተዋል። በ2018 ጋዜጠኛ ጀማል ካሹጌን እንዲገደል ትእዛዝ ሰቷል በሚል ዓለም ሁሉ አውግዟቸው የነበሩት አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢንሳልን ዲፕሎማሲያዊ መገለሉን ለመላቀቅ ልዩ ልዩ ተግባራትን አከናውነዋል። ከኢራን ጋር ለመታረቅ ቻይናን ምልጃ ላኩ። በሶሪያ ውስጥ መንግስት እንዲፈጠር እና በሀገሪቱ ላይ የተጣለው የአሜሪካ ማዕቀብ እንዲነሳ ለማድረግ ተጉ። ይሄኛው ሙከራ ከዚህ በፊት በእምሬቶች ተሞክሮ የነበረ መሆኑ ደግሞ ለየት ያደርገዋል። ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ለመጀመርም አሜሪካን ጣልቃ እንድትገባ ጋበዙ ይህንንም እምሬቶች ከዚያም በፊት የፈጸመችው ነበር። በሱዳን ጦርነት ውስጥ የሳውዲ መሃመድ የሰላም እጃቸውን በአንድ ወገን ሌላኛውን ደግሞ እሳት በሌላ መዳፋቸው ዘርግተው የመሬቶቹ መሀመድ በአንጻሩ ሙሉ ጊዜያቸውን ለጠመንጃ መድበው በውክልና እየተፋለሙ ቀጠሉ። የአዲስ
15:42 አበባውን አገዛዝ መሀመድ ቢንዛይድ እየደገፉት መሀመድ ቢንሳልን ደግሞ ክፉም ደግም ቃል ሳይወጣቸው አመታት ሄዱ። እዚህ ጋር አንድ ነጥብ እናንሳና ቀጠሮ የያዝበት እምሬትስ በገባችበት ቦታ ሁሉ የምትደግፈው ተገንጣዮችን እና ማዕከላዊን መንግስት የሚፋለሙ ሀገር አፍራሽ ታጣቂዎችን ነው። በኢትዮጵያ ግን መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠውን አካል ነው የምትደግፈው። ጥያቄው ለምን የሚል ይሆናል። ይህንን በቅርቡ እንመለስበታለን። የእምሬቶቹ ፕሬዝዳንት የሳውዲውን አለቃ በግልጽ ቋንቋ አስፈራርተዋቸዋል የሚለውን የጻፉት የወሊስ ዘጋቢዎቹ የምታደርገው ሁሉ ግንኙነታችንን ጣጣ ውስጥ የሚከተው ነው ሩሲያ ጋር ያለህ ቅርርብ በነዳጅ ሽያጫችን ላይ ተጽእኖ አለው ሳታማክረኝ ከኢራን ጋር ለመወዳጅት እየጣርክ ነው እናም አቁመው ሲሉም ገል ስጸዋቸዋል ይላሉ ከዚያ በኋላ
16:28 በሬያድ በተካሄደ የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ሳይሄዱ ቀሩ ሶሪያ ወደ ሊጉ እንድትመለስ ድምጽ በተሰጠበት የግንቦቱ ጉባኤም ላይ አልተሳተፉም የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺህ ወደ ሳውዲ በሄዱ ጊዜም የአቡድያው ሰው አልተሻገሩም ይህ በፍቅራቸው ዘመን ቢሆን ሲሆን ኖሮ የማይጠበቅ ነበር። በምላሹ መሃመድ ሰልማንም ኤምሬቶች ባዘጋጀችው እና ከአንድ አመት ተኩል በፊት በተካሄደው የአረብ ሊግ ጉባኤ ላይ አልተገኙም። የዚህ ሁሉ ጸብ ምንጩ ምንድን ነው የሚለው ጉዳይ የሚመልሱት የአለም ቀውሶች ተመራማሪው ዲና ኢስፋንዲያሪ የልዩነታቸው ምክንያት መሀመድ ሰልማን ከሃመድ ቢንዛይድ ጥላ ለመላቀቅ መወሰናቸው ነው ይላሉ። ላለፉት አመታት የሳውዲው መሃመድ ተማሪ የእምሬቶቹ መሃመድ ደግሞ አስተማሪ ሆነው የዘለቁበት መንገድ እንዲያበቃ አልጋ ወራሹ መወሰናቸው የግንኙነታቸውን መስመር አሳስበው ስጦታልም ይላሉ እናም እነዚህ
17:15 ሁለት ጉልበታሞች ስለተቃቀሩ የየመን ህዝብ አገሩንም ህይወቱንም ሀብቱንም እያጣ የውክልና ጦርነታቸው መፋለሚያ ሆኗል በቀጣይስ የሚለው ደግሞ በቀጣይ እንመለከተዋለን መልካሙን ሁሉ በመመኘት በዚሁ እንሰናበታለን >> [ሙዚቃ]