የትምህርት ቤት ክፍያ ተወሰነ | የቤት ዋጋ ሊጨምር? The NEW REAL ESTATE and Property Law, Investment in Business 2025

አጭር ማጠቃለያ

ይህ ቪዲዮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወቅታዊ የቢዝነስ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮችን ያቀርባል። ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • መንግስት በትምህርት ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ላይ ጣልቃ እንደሚገባ አስታውቋል።
  • ባንኮች ላይ የነበረው የብድር ገደብ እና አስገዳጅ የቦንድ ግዢ መመሪያዎች ተሻሽለዋል።
  • በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥን ለመከላከል የስካዳ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
  • ከአገር ውስጥ ምርቶች ወደ ውጭ በመላክ ከ7.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

የትምህርት ቤቶች የዋጋ ጭማሪ

መንግስት የትምህርት ቤቶች የዋጋ ጭማሪን በተመለከተ አዲስ መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መግለጫ መሰረት ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በክፍያ ጭማሪ ላይ መስማማት ካልቻሉ መንግስት ጣልቃ ይገባል። የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እንደገለፀው፣ ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪን በተመለከተ ከወላጆች ጋር መወያየት አለባቸው፣ ነገር ግን ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ የመጨረሻ ውሳኔው በመንግስት ይሰጣል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ 1227 የግል ትምህርት ቤቶች በ2018 የትምህርት ዘመን እስከ 65% ወይም 100% ድረስ የትምህርት ክፍያ እንዲጨምሩ መፈቀዱ ይታወሳል።

የባንክ ህግ ማሻሻያ

በቤት እና በመኪና ንግድ ላይ እንቅፋት የነበረው የባንክ ህግ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል። ባንኮች የገንዘብ እጥረት አለባቸው የሚል ምክንያት ሲሰጡባቸው የነበሩ አስገዳጅ የቦንድ ግዢ እና የብድር ጣሪያ ገደብን የሚደነግጉ መመሪያዎች ተነስተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እንደተናገሩት ባንኮች የተለያዩ የቦንድ ግዢዎችን እንዲፈጽሙ የሚያስገድዷቸው መመሪያዎች መሻር ጀምረዋል። በተጨማሪም ላለፉት ሁለት ዓመታት በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ገደብ ይነሳል። ባንኮች ለረጅም ዓመታት በተለያዩ መመሪያዎች ቦንድ እንዲገዙ ይገደዱ የነበረ ሲሆን ከስድስት ዓመታት በፊት ባንኮች ከሚሰጡት ብድር 27% ለልማት ባንክ በቦንድ ግዢ እንዲያውሉ ይገደዱ ነበር።

የስካዳ ቴክኖሎጂ ትግበራ

በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥን ለመከላከል የስካዳ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል። ይህ ቴክኖሎጂ የኤሌክትሪክ መስመሮችን፣ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን የሚከታተልና የሚቆጣጠር ነው። የስካዳ ስርዓት የኤሌክትሪክ መስመር ሲበላሽ ወይም የኃይል መቋረጥ ችግር ሲያጋጥም የሚያበሩ ትንንሽ መሣሪያዎች አሉት። ቀደም ሲል አንድ ባለሙያ መስመር ለመፈተሽ ማቋረጫውን ማብራት ወይም ማጥፋት እንዲሁም መቆራረጡን ለማየት በአካል ወደ እያንዳንዱ ቦታ መጓዝ ነበረበት። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ የስካዳ ቴክኖሎጂው ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ የኃይል ማሰራጫ መስመራዎችን የኦፕሬሽን ሁኔታ ከአንድ ማዕከል ሆኖ በመከታተል ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ እና የመዋዠቅ ችግር በቀላሉ ለመለየት እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እያስቻለ ነው።

የወጪ ንግድ ገቢ

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከ7.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከውጭ ንግድ መገኘቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 38ኛ መደበኛ ስብሰባ የንግድና ቅጠናዊት እስር ሚኒስቴር የ2017 በጀት አመት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይተዋል። በበጀት አመቱ መጨረሻ ከስምንት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከተሳኩ ኢኮኖሚያዊ ውጤቶች መካከል የወጪ ንግድ ዘርፍ ከፍተኛ አፈጻጸም እያስመዘገበ ነው።

Summarize any YouTube video in seconds

Get summaries like this one for any video, in your language, with the free Summ app.

Download on the Apple Store
Get it on Google Play

Transcript

YouTube Transcript Generator

0:00 መንግስት ከትምህርት ቤት የዋጋ ጭማሪ በተያያዘ አዲስ መግለጫ አወጣ። በዚህ መግለጫ መሰረት የዋጋ ጭማሪ ላይ መስማማት ካልተደረሰ መንግስት ጣልቃ እንደሚገባ ተነግሯል። በሌላ በኩል ደግሞ የቤት የመኪና ንግድ ላይ እንቅፋት ፈጥሮ የነበረው የባንክ ህግ ላይ ማሻሻያ መደረጉ ታውቋል። ባንኮች ላለባቸው የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንደ ምክንያት ሲጠቅሱ የነበሩት አስገዳጅ፣ የቦንድ ግዢ እና የብድር ጣሪያ ገደብ የሚደነግጉ መመሪያዎች ኦች መሻራቸው ታውቀዋል። ሰላም ቤተሰቦቻችን መረጃዎቹን የት ሀገር እና የት ሆናችሁ እየተከታተላችሁ እንደምትገኙ በሃሳብ መስጫ ላይ ጻፉልን። በየትኛው ጉዳይ ላይ መረጃ እንድናቀርብላችሁ እንደምትፈልጉም አሳውቁን አሁን ዝርዝር መረጃዎቹን አንድ በአንድ

0:45 ወደ እናንተ እናደርሳለን እስከ መጨረሻው አብራችሁን ቆዩ። መንግስት ከትምህርት ቤት የዋጋ ጭማሪ በተያያዘ አዲስ መግለጫ መግለጫ አወጣ በዚህ መግለጫ መሰረት የዋጋ ጭማሪ ላይ መስማማት ካልተደረሰ መንግስት ጣልቃ እንደሚገባ ተነግረዋል። ትምህርት ቤቶች ባቀረቡት የዋጋ ጭማሪ ፕሮፖዛል ላይ ከወላጆች ጋር መግባባት ላይ መድረስ ካልተቻለ መንግስት ውሳኔ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቀዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ 1227 የግል ትምህርት ቤቶች በ2018 አመተ ምህረት የትምህርት ዘመን እስከ 65 በመቶ 100 ድረስ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ

1:31 እንዲያደርጉ ፈቃድ መሰጠቱን መዘገባችን ይታወሳል። ጭማሪውን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ዙሪያ ላይ የግል ትምህርት ቤቶች ወላጆችን ለማወያየት ሲጠሩ ወላጆች በመገኘት ሊወያዩ እንደሚገባ አሳስበዋል። ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርአት ደንብ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የጸደቀ መሆኑን አስታውሶ ደንቡን መሰረት ጥረት በማድረግ መንግስታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት መደረጉን ገልጸዋል። ደንቡ ባስቀመጣቸው የክፍያ ዋጋ ጭማሪ ጣሪያዎች መሰረት ትምህርት ቤቶች ወላጆችን በመጥራት ግልጽነት የመፍጠር ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል። በውይይቱ መሰረት የክፍያ ጭማሪን በተመለከተ ወላጆች እና ትምህርት ቤቶች በጋራ በሃሳቡ

2:18 ላይ በመወያየትና በመመካከር የሚወስኑ መሆኑ ተገልጿል። ትምህርት ቤቶች ባቀረቡት የዋጋ ጭማሪ ፕሮፖዛል ላይ ከወላጆች ጋር መግባባት ላይ መድረስ ካልተቻለች በተቻለ ግን ሪፖርቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትምህርት እና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን የሚቀርብ እና በባለስልጣኑ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል ሲል ትምህርት ቢሮ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የቤት የመኪና ንግድ ላይ እንቅፋት ፈጥሮ የነበረው የባንክ ህግ ላይ ማሻሻያ መደረጉ ታውቀዋል። ባንኮች ለገጠማቸው የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንደ ምክንያት ሲጠቅሱት የነበሩት አስገዳጅ የቦንድ ግዢ እና የቦንድ ጣሪያ ገደብን የሚደነግጉ መመሪያዎች መሻራቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እንዳሉት ከሆነ ባንኮች የተለያዩ የወንድ ግዥዎችን እንዲፈጽሙ የሚያስገድዷቸው

3:05 መመሪያዎች መሻር ጀምረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ላለፉት ሁለት አመታት በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ገደብጣሪያም ይነሳል ተብለዋል። የፋይናንስ ዘርፉን የተመለከቱ በቀጣይ ይወሰዳሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተግባራት መካከል እነዚህን መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ መሻር እንደሆነም ከአቶ ማሞ ማብራሪያ ለመረዳት ተችለዋል። በዚህም መሰረት ባንኮች በአስገዳጅ ሁኔታ የሚገዙትን ቦንድ የተመለከተው መመሪያ በዚህ ወር ሲነሳ የብድር ገደቡን የተመለከተው መመሪያ ደግሞ በመስከረም 2018 ዓመተ ምህረት እንደሚሰረስ ታውቋል። ባንኮች ለረጅም አመታት በተለያዩ መመሪያዎች በአስገዳጅነት በወንድ ሲገዙ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከስድስት አመታት በፊት ባንኮች ከሚሰጡት ብድር 27 በመቶውን በማስላት ለልማት ባንክ በወንድ ግዜ እንዲያውሉም ይገደዱ ነበር። ይህንን መመሪያ ለማስቀረት በተደረገ ጥረት ሊሻር

3:53 ቢችልም ባንኮች የቦንድ ግዢ እንዲፈጽሙ የሚል የሚያስገድ ሌላ መመሪያ ተግባራዊ ተደርጎም ቆይቷል። በሌላ መንገድ ስራ ላይ የዋለው አስገዳጅ የወንድ ግዥ መመሪያ ባንኮች ከሚሰጡት ከእያንዳንዱ ብድር 20 በመቶን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ቦንድ ግዢ እንዲያውሉ ያስገድዳል። ሁለተኛው የቦንድ ግዥ መመሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንድ ሲሆን እያንዳንዱ ባንክ ከአመታዊ የብድር ክምችቱ ላይ አንድ በመቶ ለዚህ ቦንድ ግዢ ያውላል። በሁለቱ የቦንድ አይነቶች ባንኮች በየአመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የቦንድ ግዥ እንዲፈጽሙ ሲገደዱ ቆይተዋል።ከዛ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሰማነው ብዙዎቹ ባንኮች አሁን እያጋጠማቸው ላለው የጥሬ ገንዘብ እጥረት አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት በነዚህ በወንዶች ግዢ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ተይዞባቸው የሚቆይ በመሆኑ ነው። ውሳኔው ባንኮቹ ያለባቸውን የጥሬ ገንዘብ ችግር ለማቃለል

4:42 ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል። በተመሳሳይ ባንኮች ተጥሎባቸው የቆየው የብድር ገደብም ከተነሳ እንደቀድሞ በአቅማቸው ልክ ብድር ለማቅረብ የሚያስችላቸው እንደሚሆንም ታውቀዋል። በተለይ ለወንድ ግዢ ሲያውሉት የነበረው ገንዘብ ገንዘብ ይመለሳል ተብሎ በመመሪያው ከተደነገው ከአምስት አመታት በፊት የሚለቀቅ ከሆነ የባንኮችን የማበደር አቅም ከመጨመር ባለፈ የጥሬ ገንዘብ እጥረታቸውንም ለማቃለል ሊያግዛቸው የሚችል መሆኑ ነው የተነገረው። የባንኮችን የብድር መጠን የሚገድበው መመሪያ መጀመሪያ ሲወጣ አመታዊ የብድር ምጣኔያቸው ከ 14% መብለጥ እንደማይኖርበት ተደንግጎ ነበር። በቅርቡ መመሪያው ተሻሽሎ አመታዊ የብድር ምጣኔ እድገቱ ከ18 በመቶ መብለጥ እንደማይኖርበት ተደንግጎ በዚሁ መሰረት ሲሰሩ ቆይታ ከመስከረም 2018 ዓመት ምህረት በኋላ ግን ይህ የብድር ገደብ

5:30 እንደሚነሳ መገለጹ ለባንክ ሃላፊዎች እንደ መልካም የሚታይ እርምጃ ሆነዋል። ከእርምጃዎቹ ባሻገር የብድር ጣሪያ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በተመለከተም ባንኮች ሙሉ በሙሉ ወደ ዋጋ ተኮር ስርአት የሚገቡበት አሰራር እንደሚዘረጋ የብሄራዊ ባንክ ገዢው ማብራሪያ አመልክቷል። ይህ የብድር ጣሪያ ገደብ በቤትና በሌሎች ንብረት ግዢዎች ላይ ጫና ማሳደሩ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲገለጽ ቆይተዋል። በገደቡ ምክንያት የቤት የቤት ገዢዎች ቁጥር በመቀነሱ የቤት ዋጋ እየቀነሰ ነው የሚሉ አስተያየቶችም ተደጋግመው ሲደመጡ ቆይተዋል። በተቃራኒው ደግሞ የብድር ጣሪያ ገደቡ መነሳቱ የቤትንና የሌሎች ንብረቶችን ዋጋ ሊያኖረው ይችላል የሚል ስጋትም ተፈጥረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ለአሂል መቋረጥ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እስከዳ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ተገለጸ።

6:17 በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ለሚፈጠር የሃይል መቋረጥ ፈጣን ህጻን ምላሽ ለመስጠት የስካዳ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። በአገልግሎቱ የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አንብራር እንደተናገሩት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ የሚያጋጥሙ የአይል መቆራረጥ ችግሮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ፈጣን ምላሽና መፍትሄ ለመስጠት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ተቋማዊ እቅዱን መሰረት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ለሃይል መቋረጥ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እስከዳ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አስታውቀዋል። የስካዳ ስርዓት የኤሌክትሪክ መስመሮችን የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን የሃይል ማሰራጫ መስመሮች እና የሃይል

7:03 ማገናኛና ማቋረጫዊ ስራ ላይ መሆናቸውን የሚከታተል የሚቆጣጠር እና መረጃ የሚሰጥ ቴክኖሎጂ መሆኑን ገልጸው ይህም በኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እና መተላለፊያ መስመሮች ላይ ለሚፈጠር የሃይል መቋረጥ ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስችላል ብለዋል። አቶ አንዳሉት የስካዳ ቴክኖሎጂው የኤሌክትሪክ መስመር ሲበላሽ እና መስመሩ በየሃይል መቋረጥ ችግር ሲያጋጥም የሚያበሩ ትንንሽ መሳሪያዎች አሉት። በእነዚህ መሳሪያዎች አማካኝነት ችግር ያጋጠመው የኤሌክትሪክ መስመር በቀላሉ ለመለየት ብሎም በፍጥነት አገልግሎት እንዲጀምር ያደርጋል። ከሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ዝቅተኛ መስመሮች ድረስ የተዘረጋውን መስመር የሃይል ስርጭትን ለመቆጣጠር ኔትዎርኩ ላይ የተገጠሙ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን ደህንነታቸውን ለመፈተሽ እና የቁጥጥር ስራ ለመስራትም ያስችላል።

7:48 በተጨማሪም የሃይል ማብሪያና ማጥፊያ ወይም ስዊችንንግ ስቴሽን እና ስዊች ጊር ላይ የኤሌክትሪክ ፍሰቱን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል የሚያገለግሉ ጣቢያዎችን በቀላሉ ለመቆጣጠር የሚያግዝ መሆኑንም ገልጸዋል። ቀደም ሲል አንድ ባለሙያ መስመር ለመፈተሽ ማቋረጫውን ማብራት ወይም ማጥፋት እንዲሁም ደግሞ መቆራረጡን ለማየት ሲፈልግ በአካል ወደ እያንዳንዱ ቦታ መጓዝ ነበረበት። ይህ አሰራር ጊዜ የሚፈጅ ቀልጣፋ ያልሆነ እና አደገኛ አሰራር መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በመጥፎ የአየር ሁኔታ ድንገተኛ አደጋዎች ያስከትላል የሚሉት ስራ አስፈጻሚው የስካዳ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መደረጉ ሁሉንም ችግር በማስቀረት ፈጣን እና ምቹ አሰራርን ማምጣት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል። ይህ ሽግግር ፈጣን እና ትክክለኛ የስራ ሂደቶች እንዲኖሩ ከማስቻሉም በላይ ለወደፊት

8:34 የስማርት ግሪድ መስፋፋትን የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ የስካዳ ቴክኖሎጂው ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ተከትሎ የሃይል ማሰራጫ መስመራዎችን የኦፕሬሽን ሁኔታን ከአንድ ማዕከል ሆኖ በመከታተል ሊከሰት የሚችለውን የሃይል መቆራረጥ እና መዋጀ ችግር በቀላሉ ለመለየት እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እያስቻለ ነው ብለዋል። በከተማዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ መስመሮችን የማሻሻል ስራው በከፍተኛ ፍጥነት ተጠናቆ ወደ ሙሉ የስካዳ ዲስትሪውሽን ማኔጅመንት ሲስተም ለመግባት እየተሰራ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው በቅርብ ጊዜያት አጠቃላይ ስራውን በማጠናቀቅ አስተማማኝነትን ደህንነትን እና ቅልጥፍናን በማምጣት ጠንካራ የዲጂታል ብሮድ ባንድ የግንኙነት አውታር ይፈጥራል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስካዳ

9:22 ቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ የመጀመሪያ ዙር አዲስ አበባን ጨምሮ በስምንት ዋና ዋና ከተሞች ማለትን በባህር ዳር በደሴ በመቀሌ በአዳማ በድሬደዋ በሃዋሳ እና በጅማ ከተሞች የሙከራ ስራ መሰራቱን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያሳያል በሁለተኛው ዙር የስካዳ ቴክኖሎጂ ትግበራ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ታውቀዋል በሌላ በኩል ደግሞ ከወጪ ንግድ ከ72 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ታወቀ በበጀት አመቱ 11 ወራት ከ7.2 ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከወጪ ንግድ መገኘቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 38ኛ መደበኛ ስብሰባ የንግድና ቅጥናዊት እስር ሚኒስቴር የ2017 በጀት አመት የ11

10:08 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይተዋል። የንግድ እና ቅጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ እንደተናገሩት በበጀት አመቱ በሀገሪቱ የወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ተገኝተዋል። ከጠቅላላ የወጪ ንግድ 4.5 5 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው በአፈጻጸም ከእቅድ በላይ 7.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል። በበጀት አመቱ መጨረሻ ከስምንት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል። በበጀት አመቱ 11 ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከ206 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር ከ3.9 9 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጭማሪ ማሳየቱንም ጠቅሰዋል። በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከተሳኩ ኢኮኖሚያዊ ውጤቶች መካከል የወጪ ንግድ ዘርፍ ከፍተኛ አፈጻጸም እየተመዘገበበት መሆኑን አክለዋል። በወጪ ንግድ

10:56 ምቹ ምህዳር መፈጠሩ የተለያዩ የህግ እና አሰራር ማነቆዎች መፈታታቸው ከላኪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በተሻለ ቅንጅት በመሰራቱ በሃገሪቱ ታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ማግኘት ተችለዋል ብለዋል። ክቡራት እና ክቡራን የአዲስ ቢዝነስ የዩቲዩብ ቻናል ተከታታዮቻችን ችን ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ ሳታደርጉ የምትከታተሉን ከሆነ ቢዝነስ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ አዳዲስ መረጃ ለማግኘት የዩትዩብ ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ በትህትና እንጠይቃለን። እነ

Share

YouTube Video Summaries